ማዕከሉን የመረቁት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ናቸው።
የተሻለ ህክምና ፍላጋ ወደተለያዩ ሀገራት ከኢትዮጵያ በሚደረግ ጉዞ በአመት ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚወጣ በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ ተነግሯል።
አብዛኛው የውጭ ሀገር ህክምና ጉዞ ሙሉ የጤና ምርመራ ለማድረግ እና የካንሰር ህክምና ፍለጋ መሆኑ ተጠቅሷል።
ሀባሪ ሜዲካል ፕላዛ የተቋቋመውም ይህንን በህክምና ምክንያት ወደ ወጪ ሀገር የሚደረግን ጉዞ ማሰቀረት ብሎም ከጎረቤት ሀገራት ታካሚዎችን ለመሳብና አዲስ አበባን የህክምና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ነው ሲሉ የማዕከሉ መስራችና ባለቤት ዶ/ር አከዛ ጣዕመ ተናግረዋል።
በስነስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አደነች አበቤ በከተማዋ ያለውን የጤና አቅርቦት ለማሳደግ መንግስት ነባሮቹን የጤና ተቋማት አቅማቸውን ማሳደግ ላይ እንዲሁም አዳዲስ ሆስፒታሎች ግንባታ እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
በዚህም ሶስት አዳዲስ ሆስፒታሎች እየተገነቡ መሆኑን ተናግረው በዚህም የግሉ ዘርፍ አብሮ እንዲሰራ ጠይቀዋል።
ዛሬ የተመረቀው ሀባሪ ሜዲካል ፕላዛ አይነት ተቋማት በብዛት እንደሚያስፈልጉ አስረድተዋል ።
የውስጥ ደዌ፣ የህፃናት፣ የማህፀን እና የፅንስ፣ የቆዳ ህክም፣ የልብና ሌሎች ህክምናዎችን ጨምሮ 15 ስፔሻሊስት ህክምናዎች እንደሚሰጥ የተናገረው ሀባሪ ሜዲካል ፕላዛ የቪአይፒ የህክምና ፓኬጆች ማሰናዳቱንም ተናግሯል።
ማዕከሉ ሙሉ ለሙሉ ተመላላሽ ታካሚዎች የሚያስተናግድ ሲሆን ተኝቶ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሲኖሩ ወደ እህት ኩባንያዎቹ አሜሪካን ሜዲካል ፣ሰማሪታን ሰርጀሪካል ሴንተር እና አክሶን ስትሮክ እና ስፓይን ሴንተር እንደሚልክ ዶ/ር አከዛ አስረድተዋል።
ሀባሪ ሜዲካል ፕላዛ 500 መቶ ሚሊየን ብር ኢንቨስት አድረጉ ስራ መጀመሩን ሰምተናል።
ሀባሪ ሜዲካል ፕላዛ የተከፈተው በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ አቅራቢያ ኖክ ሕንፃ ላይ ነው።
ሸገር 102.1 ንጋቱ ሙሉ
