Home ዜና “ለድርድር ዝግጁ ነኝ” ሩስያ

“ለድርድር ዝግጁ ነኝ” ሩስያ

“ለድርድር ዝግጁ ነኝ” ሩስያ

የሩስያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ሞስኮ ከኬይቭ ጋር ለመስማማት ዝግጁ ናት አሉ፡፡

ሩስያ የፊታችን ሰኞ በቱርክ ኢስታንቡል ለሚደረገው  ሁለተኛ  ዙር የሰላም ንግግር የዩክሬንን መልስ እየጠበቅች እንደሆነም ይፋ አድርጋለች ፡፡

ሰርጌይ ላቭሮቭ ከአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በስልክ ቆይታ ማድረጋቸውን ገልጸው፤ ለንግግሩ ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቀዋል ፡፡

ሩቢዮ በበኩላቸው፤ ዋሽንግተን በሁለቱ ሀገራት ለሚደረገው የሰላም ውይይት እንደ ድልድይ ለማገልገል ዝግጁ መሆኗንም ተናግሯል፡፡

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲብ ጠይብ ኤርዶሃንም የሩስያን የሰላም እቅድ በደስታ እንደተቀበሉት እና ሀገራቸው ለዚህ ድርድር መሳካት የበኩሏን እንደምታደርግ ገልጸዋል፡፡

Nbc_Ethiopia