መላኩ በላይ የክብር ሜዳሊያ ተሸለመ

Date:

ዓለም አቀፍ ዝናን ያተረፈው ኢትዮጵያዊው የዳንስ ባለሙያ እና የፈንድቃ ባህል ማዕከል መስራች መላኩ በላይ፤ ከፈረንሳይ መንግሥት የተሰጠውን ከፍተኛ የክብር ሜዳሊያ ሽልማት በክብር ተቀብሏል።

ባለሙያው የፈረንሳይን “ኦፊሴር ዴ ላ ኦርደሬ ዴስ አርትስ እና ዴስ ሌትረስ” (Officier de l’Ordre des Arts et des Lettres) ሜዳሊያ የተቀበለው በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ከሆነው ሬሚ ማሬሾ (Rémi Maréchaux) እጅ ነው።

ይህ የክብር ሜዳሊያ በስነ-ጥበብ እና በስነ-ጽሁፍ ዘርፍ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦች የሚሰጥ ከፍተኛ ዕውቅና ነው።

ሽልማቱን በተቀበለበት ወቅት መላኩ በላይ ባስተላለፈው መልዕክት፤ የተሰማውን ጥልቅ ደስታ ገልጾ ሽልማቱ የጋራ ስኬት መሆኑን ተናግሯል፦”ይህ ክብር እኔን እና ፈንድቃን ለደገፉን ሁሉ ነው” ያለ ሲሆን፤ በአለም ዙሪያ ያሉ ታዳሚዎች በፈንድቃ ላይ ላሳዩት እምነት ምስጋና አቅርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...

ከአሜሪካ ጋር የሚኖረው “የጨዋታው ሕግ ተቀይሯል፤ የተመጣጠነ ምላሽ ዘመን አብቅቷል

ኢራን ከአሜሪካ በኩል ለሚሰነዘርባት ጥቃት የምትሰጠው ተመጣጣኝ የአጸፋ ምላሽ...

የ2.5 ቢሊየን ብር ግዙፍ ፕሮጀክት በአታ ለማርያም ገዳም በመስከረም ወር የመሠረት ድንጋይ ሊያኖር ነዉ

​በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ የታዕካ ነገሥት...

የዲቪ ዕድለኞች የማመልከቻ ሂደታቸውን እንዲቀጥሉ ተወሰነ!

የአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት በዲቪ ሎተሪ አመልካቾች የማመልከቻ ሂደት...