ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በአዲስ አበባ 5 ዘመናዊ  ሆቴሎችን ሊገነባ ነው

Date:

ሆቴሎቹ ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው 32ተኛው የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሸራተን አዲስ ኤሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ እጅግ ዘመናዊ የሆነና የሸራተን አዲስ ሆቴልን ስያሜ የሚይዝ ሌላ ሆቴል ይገነባል። በሚሊኒየም አዳራሽ ቅጥር ግቢ ዘመናዊ ሆቴል(Moxy by Marriott)፣በመሀመድያ የመኖሪያ መንደር (Four Points by Sheraton) ሆቴሎች ይገነባሉ።
በቅርቡ የሚድሮክን ቤተሰብ የተላቀለው ዋቢሸበሌ ሆቴል(autograph collection by Marriot) ደረጃ ለጉባኤው ዝግጁ ይሆናል።

አፍሪካ ህብረት አጠገብ እየተገነባ ያለው ዌስት ኢን አዲስ(Westin Addis) ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል። ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለ32ተኛው የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ተሳታፊዎች 1500 አልጋ ያላቸው ሆቴሎችን እንደሚገነባ የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ በቅርቡ መናገራቸው ይታወሳል።

በተጨማሪም ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  በክልል ከተሞች በጂማ እና ሃዋሳ (Four Points by Sheraton) ሆቴሎችን እየገነባ ይገኛል።
በባህርዳር ከተማ ደግሞ(Four Points by Sheraton) እና (Protea by Marriot) ለመገንባት ዝግጅቱን አጠናቋል ።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በቅርቡ የላንጋኖ ሳቫና ሪዞርትን በግዥ የተረከበው ሲሆን በማርዮት ብራንዶች አለም አቀፍ ሪዞርት በመገንባት ወደ ስራ ይገባል። ባሳለፍነው ሳምንት የኤኮ ቱሪዝም ዘርፉን ከፍ ሊያደርግ የሚችለውን የደንቢ ኤኮ ሎጅ በማስመረቅ ወደ ስራ አስገብቷል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

መልካም አዲስ ዓመት

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!! እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ...

ከቀደመው ስሕተታችን ተጸጽተን ንስሐ ከገባን እግዚአብሔር ከኛ የሚፈልገውን አግኝቶአል ማለት ነው

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ...

ዩጋንዳ በቀጣዩ ዓመት መጀመሪያ የአለም አዲስ የነዳጅ ላኪ ሀገር ልትሆን ነው

ዩጋንዳ በፈረንጆቹ 2027 መጀመሪያ ላይ ከአልበርቲን ግራበን ማዕድን ማውጫ...

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት ገለጸች

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት የአገሪቱ...