‘ምዕራባውያን እረፉ’ ሩሲያ

Date:


ሩሲያ እና ዩክሬን ወደ ሰላም ስምምነት ከደረሱ በኋላ ሰላም አስከባሪ ሀይል ወደ ዩክሬን ይላካል መባሉ ሞስኮን ማስቆጣቱ ታውቋል።

እንግሊዝ እና ፈረንሳይ መራሹ የፍቃደኞች ጥምረት በፓሪስ በዩክሬን ጉዳይ ከተወያየ በኋላ ወደ ዩክሬን ወታደር እንደሚልኩ መስማማታቸው ይታወሳል።

የሩሲያ ባለስልጣናት ግን የፍቃደኞች ጥምረት ውሳኔ የሰላም ጥረቱን የሚያከሽፍ ነው ሲሉ ነቅፈዋል ።

የትኛውም የውጭ ሀይል ወደ ዩክሬን የሚገባ ከሆነ ቀዳሚ ኢላማ እናደርገዋለን ሲሉም የክሬምሊን ባለስልጣናት ከወዲሁ እያስጠነቀቁ ነው።

የሞስኮ ዛቻም የተሰማው፣ እንግሊዝና ፈረንሳይ ዓለም አቀፍ የሰላም አስከባሪ ሀይል ወደ ኬይቭ መላካቸው እንደማይቀር ከገለፁ በኋላ ነው።

ምዕራባውያን ከዚህ ድርጊታቸው የማይቆጠቡ ከሆነ ከባድ ኪሳራ ይደርስባቸዋል ስትል ሩሲያ መግለጫ ሰጥታለች።

በሌላ በኩል የሩሲያ ድሮኖች በዲኒፕሮ ግዛት ጥቃት ፈፅመው ከ800 ሺህ እስከ 1 ሚሊዮን ህዝብ ከመብራት ውጭ መሆኑን የኬይቭ ባለስልጣናት ተናግረዋል።

ከዚህ ጥቃት ጋር በተያያዘ ዘለንስኪም የሩሲያ ጥቃት ሊቀጥል እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል ።
ቲ አርቲ ወርልድ እንደዘገበው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ይህንዓለም አቅናው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ እና ከፍተኛ የባለአክስዮኖች ቁጥር ካላቸው...

ማዕቀቦች የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ቢያደናቅፉም መንግስቱን ሊጥሉ እንደማይችሉ ተገለጸ

ማዕቀቦች የኢራንን ወታደራዊ እና የኒውክሌር እንቅስቃሴዎች አስቸጋሪና ውድ እንዲሆኑ...

የአፍሪካ ሀገራት አዲስ የኢንቨስትመንት ፈንድ ይፋ አደረጉ

በአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ የብድር ጫና ለማቃለል እና...

ዶናልድ ትራምፕ “በቅርቡ” ሆርሙዝ የአሜሪካ ግዛት አካል እንደሚሆን ተናገሩ

ከኢራን ጋር ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካው...