ሰይፉ ፋንታሁን ( የማናውቀው ሰው ) በነጻነት ወርቅነህ ቀብር ላይ እንዲናገር ተጠርቶ ለምን ፈቃደኛ ሳይሆን ቀረ ?

Date:

ነጻነትን ወደ ሕይወት ለመመለስ ጥሯል ። አልተሳካለትም ።

 ምክንያቱን ለማወቅ ፍላጎት የለኝም ። አልጠይቅም ። ደግሞም አይነግረኝም ። ሰይፉን የምታውቁት የመሰላችሁ ብዙዎቻችሁ ተሳስታችኋል ። የሚያውቁት ጥቂቶች ይኖራሉ ። ካሁን ቀደምም እንዳልኩት ሰይፉ ፋንታሁን ቀልዱ ቁምነገሩን የሸፈነበት ሰው ነው ። " ቧልተኛ " ነው ሰይፉ ። አንዳንዴ በትልቅ ቁምነገር ሳይቀር ይቧልታል ። " ምን ሆኗል ? "ም እንለዋለን ። ገፋ ሲልም እንጽፍበታለን ። እሱ ይቀጥላል ። ብዙውን ጊዜ ግን ( አልታደልን ይሆናል ) መልካምነቱን አናወራለትም ። ደግሞስ ከየት አምጥተን እናውራለት ? እንደ ሀገር ወግ ልማድ ፣ እንደ ዘመኑ ቋንቋ አይናገር ። ግራው ሲሰጥ ቀኙ አይቀርጽ ። ወይም ደግሞ አድርጎ እሱ እንዳልፈለገ አድርጎ በጎን አይናገር ። ከሁሉም በላይ ሰይፉ የሰው ስቃይ ላይ አይጨፍርም ። ያጣ ሰውን ክብር አይነፍግም ። ሚሊዮን ብርን አሰጥቶም በሰው ላይ አይፎክርም ። እንደ ቀልድ እልፍ ነው የሚለው ። ሰውን መርዳት ላይ በትክክልም የክርስትናን መርህ የሚከተል ነው ። " አንድ ስሜ አይጠቀስ ያለ ወዳጄ ከአሜሪካ ከዳርፉር .  .  . " የሚለው ብዙውን ጊዜ ውሸቱን ነው ። ራሱ ነው የሚያደርገው ። አንዳንዴ እውነት ይሆናል ። ወደ ዋናው ጉዳይ ልመለስ ።

  የዛሬ ዓመት ገደማ ነጻነት ወርቅነህ ታሞ ህንድ ሀገር ሲሄድ ሰይፉ ፋንታሁን 1,000,000:00 ገደማ ( ቢበልጥ እንጂ አያንስም ) ሰጥቷል ። ከጥቂት ወራት በፊትም ኢትዮ አሜሪካዊት ሀኪም ከአሜሪካ አስመጥቶ ( በራሷ መጥታም ይሆናል ) የሚከፈለውን ከፍሎ አሳክሞታል ። " የሚያስፈልግ ወጪ ካለ እኔ አመጣለሁ " ብሎ ነጻነት ራሱን አረጋግቶ ህክምናውን እንዲከታተል ሞክሯል ፤ ነግሯል ፤ ለምኗል ። የነጻነት መጨረሻ ይህ እንዳይሆን ሰይፉ ፋንታሁን ጥሯል ። ሰይፉ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ጥቂት ሰዎችም ( " እገሌና እገሌ " የማልላቸው ) ሰዎችም ነጻነት ወደ ሕይወት እንዲመለስ ፣ ለልጆቹ መኖሩ እንዲቀጥል ፣ ሕዝብም እንዲህ እንዳይሰበር ለማድረግ የጣሩ ነበሩ ። እነዚያ ሰዎች ዛሬ በቀብሩ ፊት ላይ የሉም ። እንዳይሆኑ ተከልክለው አይመስለኝም ። 

   እንዲሆን የፈለጉት ባለመሆኑ ልባቸው ተሰብሮ ይመስለኛል ። ቁጭት ይኖርባቸዋል ፤ ፀፀት ግን ሌሎች ጋ እንጂ እነሱ ጋ የለም ። ሰይፉ ፋንታሁንን ወደ መድረክ አስወጥቶ ያላናገረው ይህ ቁጭት ይመስለኛል ። ልፋቱ መና መቅረቱ ፣ ያሰበው አለመሆኑ ይሆናል ። ወይም ሌላ ይሆናል ። ብቻ ሰይፉ ፋንታሁን ( እና ሌሎች ጥቂት ወዳጆቹ ) ዛሬ የነጻነት ወርቅነህ ቀብር እንዳይሆን የቻለውን  ያህል ( ከዚያም አለፍ ብሎ ) አድርጓል ። ባይፀፅተውም ግን ይቆጨዋል ። ያሰቡት ፣ የሞከሩት ሳይሆን ሲቀር ይቆጫል ። ሰይፉም ሊቆጨው ይችላል ። "*እንዲህ ማድረግ ሲገባኝ አላደረኩም " ወይም " ማድረግ ሳይገባኝ አድርጌያለሁ " የማለት ፀፀት ግን አይኖርበትም ። ሌሎች ደግሞ በአንጻሩ ጸጸት ይኖርባቸው ይሆናል ። እሱ ይቆይ ። ወዳጄ ሰይፉ ፋንታሁን ለነጻነት ወርቅነህ አድርገህ ላልተናገርከው ፣ ለሌሎች በምሥጢር ደብቀህ ለምታደርገው ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ ። የተደበቀን የሚገልጥ አምላክ ይይህ ፤ ያወጣኸው ሁሉ በብዙ እጥፍ በዓለም ይመለስ ።

    ለመደምደሚያ እንዲሆን  ከዚህ ቀደም ብዬ የለጠፍኩትን እዚህ ልድገመው ።

            " በነገራችሁ ላይ ፦ በቀብራችሁ ላይ ማቅ ለብሰው  ከተገኙት ያልተገኙት ፣ ፀጉራቸውን እየነጩ ካለቀሱት ዝም ያሉት የእናንተ ጠቃሚ  የሕይወት ወዳጆች ሊሆኑ ይችላሉ። ችግሩ ግን ሳትረዷቸው አልፋችኋል  "
(ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...

ከአሜሪካ ጋር የሚኖረው “የጨዋታው ሕግ ተቀይሯል፤ የተመጣጠነ ምላሽ ዘመን አብቅቷል

ኢራን ከአሜሪካ በኩል ለሚሰነዘርባት ጥቃት የምትሰጠው ተመጣጣኝ የአጸፋ ምላሽ...

የ2.5 ቢሊየን ብር ግዙፍ ፕሮጀክት በአታ ለማርያም ገዳም በመስከረም ወር የመሠረት ድንጋይ ሊያኖር ነዉ

​በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ የታዕካ ነገሥት...

የዲቪ ዕድለኞች የማመልከቻ ሂደታቸውን እንዲቀጥሉ ተወሰነ!

የአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት በዲቪ ሎተሪ አመልካቾች የማመልከቻ ሂደት...