የዓለማችን ታዋቂው የዜና ማሰራጫ ሲኤንኤን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን አስደናቂ የዕድገት ጉዞ በሰፊው ዘገበ።
በ12.5 ቢሊዮን ዶላር በቢሾፍቱ ከተማ እየተገነባ ያለው ግዙፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ በዓመት እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ ከፍተኛ አቅም እንደሚኖረው ዘገባው አሳይቷል።
ይህ ዘመናዊ ፕሮጀክት አፍሪካውያንን በአንድነት በማስተሳሰር እና የአህጉሪቱን ነፃ ንግድ ለማፋጠን ትልቅ ሚና እንዳለው ተገልጿል።
ይህ ግዙፍ የልማት ሥራ ኢትዮጵያን የዓለም አቀፍ ትስስር እና የንግድ ማዕከል እንደሚያደርጋት ሲኤንኤን አመልክቷል።
አየር መንገዱ ከአቪየሽን ሥራው ጎን ለጎን የኢትዮጵያን ውብ ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ሀብቶች ለዓለም በማስተዋወቅ የቱሪዝም ገቢዋ እንዲያድግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ዘገባው ጠቁሟል፡፡
