🔸 ትላንት ምሽት ከኢራን ግዛት የተተኮሰ የሮኬት ጥቃት በሰሜናዊ እስራኤል ማረፉን የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
🔸 ከጥቂት ገዜ በኋላ የኻታም አል-አንቢያ ዕዝ ጥቃቶቹ እስራኤል በሊባኖስ ላይ ለፈጸመችው ተከታታይ ድብደባ የተሰጡ ምላሾች መሆናቸውን አስታውቋል።
🔸 የኢራን ጥቃቶችን ተከትሎ የእስራኤል ብሔራዊ ደህንነት ሚኒስትር ቤን-ግቪር ምላሽ እንደሚሰጥ አስጥንቅቀዋል።
🔸 እስራኤል የአጸፋ የአየር ጥቃቶችን ሰንዝራለች። ኢርና የዜና ወኪል እንደዘገበው በቴህራን ቢያንስ ሁለት ከባድ ፍንዳታዎች ተከስተዋል። የአካባቢው ባለሥልጣናት የታብሪዝ መካከለኛ ክፍልም ጥቃት እንደደረሰበት ገልጸዋል። በተጨማሪም የኹዜስታን ግዛት ባለሥልጣናት በካሩን ኬሚካል ፋብሪካ ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቀዋል።
🔸 የኢራን አብዮታዊ ዘብ በሁለት ዋና ዋና የእስራኤል የአየር ኃይል ካምፖች — ቴል ኖፍ እና ኔቫቲም ላይ “ናስር” በተሰኘ ወታደራዊ ዘመቻ ለጥቃቶቹ ምላሽ እንደሚሰጥ አስታውቋል።
🔸 የ “አንሳር አላህ” (ሁቲ) ንቅናቄ ለኢራን ያለውን ድጋፍ በመግለጽ፤ የእስራኤል መርከቦች በቀይ ባሕር በኩል እንዳያልፉ እገዳ መጣሉን አስታውቋል።
🔸 ውጥረቱ እየተባባሰ መምጣቱን ተከትሎ የኢራቅ ባለሥልጣናት የሀገሪቱን የአየር ክልል ለ72 ሰዓታት መዝጋታቸውን አስታውቀዋል። ሶሪያም ከኢራን የተተኮሱ ሚሳኤሎችን በአየር ላይ ለማክሸፍ በተደረገው ሙከራ በዋና ከተማዋ ሰማይ ላይ ፍንዳታዎች ከተሰሙ በኋላ የደማስቆ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲሁም በሀገሪቱ ደቡባዊ ክፍል ያለው የአየር ክልል ለ12 ሰዓታት መዘጋቱን ገልጻለች።
