ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት በመሆን በድጋሜ መመረጣቸውን ጠቅላይ ምክር ቤቱ አስታወቀ።
” ምርጫችን በመስጂዳችን ” በሚል ትላንት ጀምሮ በተካሄደው ምርጫ ጠቅላይ ም/ቤቱን ለ5 ዓመታት የሚመሩ ከፍተኛ አመራሮች እና ስራ አስፈፃሚ አባላት ታውቀዋል ተብሏል።
ከሰኔ 12፣ ጅምሮ በየመስጂዱ ምዝገባ ሲከናወን ቆይቶ ከ13 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ሰው ተመዝግቦ ከትግራይ ክልል ውጭ በመላው ሀገሪቱ ከነሃሴ 9 እስከ 30 ፣2017 ዓ.ል ድረስ ድምፅ የመስጠት ሂደት ከተከናወነ በኋላ ከወረዳ ጀምሮ በየደረጃው ምክርቤቶች ተመስርተው ለቀጣዩ እርከን ተወካዬች እንደተመረጡ ተገልጿል።
የተመሰረተው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ጠቅላላ ጉባኤ 195 አባላት ያሉትና ከየዘርፉ ክልሎቹን የወከሉ ሁሉ የተካተቱበት እንደሆነ ተገልጿል።
በትግራይ ክልል ምርጫ ለማካሄድ አመች ሁኔታ ባለመኖሩ ምክንያት ምርጫ ባለመካሄዱ በጠቅላላ ጉባኤ በፀደቀው መሰረት በፌደራል መጅሊስ ያለው ውክልና ባለበት የሚቆይ ይሆናል ተብሏል።
እነማን ተመረጡ ?
- የክቡር ዶክተር ሼይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ – ፕሬዝዳንት
- ሼይኽ አብዱልከሪም ሼይኽ በድረዲን- ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት
- ሼይኽ ጁነይድ ሀምዛ-ምክትል ፕሬዝዳንት
- ሼይኽ ሀሚድ ሙሳ- ምክትል ፕሬዝዳንት
- ዑስታዝ ተምኪን አብዱላሂ- ዋና ፀሀፊ (ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ) ምሁር
- ሸይኽ አሚን ኢብሮ-የስራ አስፈፃሚ አባል (ከድሬዳዋ )
- ዶ/ር ሙሐመድ ሳሊህ – የስራ አስፈፃሚ አባል (ከኦሮሚያ)
- ሸይኽ ሙሐመድ አሚን አያሽ – የስራ አስፈፃሚ አባል (ከሐረሪ)
- ሸይኽ ሙሐመድ አህመድ ያሲን የስራ አስፈፃሚ አባል (ከአፋር)
- ሸይኽ ኢድሪስ ደጋን- የስራ አስፈፃሚ አባል (ከአማራ ክልል)
- ዑስታዝ ፋሪስ ግርማ- የስራ አስፈፃሚ አባል (ከደቡብ ምዕራብ) ምሁር
- ዑስታዝ ፋይሰል ኢማም – የስራ አስፈፃሚ አባል (ከጋምቤላ) ምሁር
- ዑስታዝ ፋሪስ ጀማል – የስራ አስፈፃሚ አባል (ከደቡብ ኢትዮጵያ) ምሁር እና
14- ዑስታዝ ሽኩር ቃሲም- የስራ አስፈፃሚ አባል (ከሲዳማ ክልል) ምሁር
15 ኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ (ትግራይ) ምሁር ሆነው መመረጣቸውን ምክር ቤቱ አሳውቋል።
በተጨማሪም 7 አባላት ያለው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዑለማ ጉባኤ አባላት የተመረጡ ሲሆን
በዚሁ መሰረት፦
- ሸይኽ አሊ መሀመድ- ሰብሳቢ
- ዶክተር ማህሙድ ሁሴን – ምክትል ሰብሳቢ
- ዶክተር መሀመድ ከማል- ጸሀፊ
- ሸይኽ ኤልያስ አህመድ -አባል
- ሸይኽ አብዱሰላም አንዋር – አባል
- ሸይኽ ዚያድ አሊይ- አባል
- ሸይኽ አድናን መሀመድ -አባል
ሆነው ተመርጠዋል።
ጠቅላይ ምክርቤቱን ለቀጣይ አምስት አመታት እንዲመሩ የተመረጡ ከፍተኛ አመራሮች በታላቁ አንዋር መስጂድ ቃለመሃላ መፈጸማቸው ተገልጿል።
@tikvahethiopia
