በመዲናዋ ኢትዮጵያዊ ምግቦች የሚቀርቡበት ፌስቲቫል ሊዘጋጅ ነው

Date:

የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ኢትዮጵያዊ ምግቦች የሚቀርቡበት ፌስቲቫል ሊያዘጋጅ መሆኑን አስታወቀ፡፡

“ጋስትሮኖሚ” የተሰኘው ፌስቲቫሉ የሚዘጋጀው የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ጎልደን ግሩፕ ሆስፒታሊቲ ከተሰኘ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው፡፡

የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ክፍት በሚሆነው በዚህ ፌስቲቫል ላይ ኢትዮጵያዊ ምግቦች፣ የምግብ ግብአት አቅራቢዎች በሆቴሎችና በዘርፉ የተሰማሩ ከ100 በላይ ድርጅቶች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽነር አቶ ሁንዴ ከበደ የጥምቀት ከተራ በአልን አስታኮ በተዘጋጀው በዚህ ፌስቲቫል ላይ በርካታ የውጭ አገር ዜጎች የሚታደሙ ሲሆን ከ20 ሺህ በላይ ሰዎችም ይጎበኙታል ተብሎ እንደሚጠበቅ መግለጻቸውን ኤ.ኤም.ኤን ዘግቧል፡፡

ፌስቲቫሉ በሚሊኒየም አዳራሽ ጥር 9 እና 10 ለሁለት ቀናት ለህዝብ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ በዘገባው ተመላክቷል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

መልካም አዲስ ዓመት!!

  ግዮን መጽሔት :-   አዲሱን የኢትዮጵያ ዓመት ስንቀበል፣ ለውዷ ኢትዮጵያችንና...

የድሬዳዋ አስተዳደር ተሿሚዎች

4ኛ የስራ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት፣ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ያካሄደዉ...

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ተሿሚዎች

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ  ክልል ምክር ቤት 7ኛ የስራ ዘመን፣ 1ኛ...

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ተሿሚዎች

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 7ኛ የስራ...