በሲዳማ ክልል ከ62% በመቶ በላይ የሚታረሰው መሬት በአሲዳማነት የተጎዳ ነዉ

Date:

በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ የሚታየው የምርታማነት ማነቆ በዋናነት የመሬት አሲዳማነት ችግር እንደሆነ መሆኑ ተገለፀ ሲሆን በተለይም በሲዳማ ክልል ከሚታረሰው መሬት ውስጥ ከ 62 በመቶ በላይ የሚሆነው በአሲዳማነት የተጎዳ መሆኑ ተጠቁሟል።

ይኸውም፣ ክልሉ ከሚያለማው 153 ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥ 95 ሺህ ሄክታሩ በአሲዳማነት የተጠቃ ነው።

የግብርናውን ዘርፍ የምርታማነት አቅም ከሚፈለገው ደረጃ እንዳይደርስ ካደረጉት ማነቆዎች አንዱ፣ ከእያንዳንዱ ሰብል የሚገኘው አማካይ ምርት ዓለም የደረሰበትን የምርታማነት ደረጃ አለመድረሱ ነው። ሞዴሎች የደረሱበትን አማካይ ምርት የማግኘት አለመቻል ትልቅ እንቅፋት ሆኖ ቀጥሏል።

​የሲዳማ ክልል ግብርና ቢሮ እንዳመለከተው ፤ እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ ማዳበሪያን ከውጭ እያስገባች ትገኛለች። ምንም እንኳን በቀጣይ አምስት ዓመታት ውስጥ የሀገሪቱ ትልቅ ፕሮጀክት የሆነው የማዳበሪያ ፋብሪካ ሲገነባ ከሀገር ውስጥ መጠቀም የሚቻልበት ዕድል ቢኖርም፣ በአሁኑ ወቅት የማዳበሪያ አቅርቦት ወሳኝ ጉዳይ ነው።

​”የሀገራችን ሰባት ሚሊዮን በላይ ሄክታር የሚሆን መሬት በአሲዳማነት የተጠቃ ነው” ያለዉ ቢሮዉ ይህ አሃዝ ካለው 32 ሚሊዮን ሄክታር የሚታረስ መሬት አኳያ ሲታይ የአሲዳማነቱ ስፋት የሀገሪቱ ትልቅ ፈተና መሆኑን ያመለክታል ሲሉ ገልጸዋል ።

capital news

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ፤ አደረሰን

ሰማያት ተከፈቱ ፣ ምስጢርም ተገለጠ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዘመዷ ቅድስት...

አባቴ ለእኔ አባት ብቻ አልነበረም፤ ለእናቴ ታማኝ ባል፣ ለሁላችንም ደግሞ የደስታ ምንጭ ነበር

"አባዬ… ዛሬ ላለሁበት ማንነት መሰረት የሆንከኝ አንተ ነህ!" ​የአርቲስት...

የአንበሶቹ ትንሳኤ፦ የዳካር እንባ እና የቴራንጋ ድል

​በዳካር ሰማይ ስር ዛሬ ጨረቃ አልወጣችም፤ ይልቁንም በሚሊዮን የሚቆጠሩ...

የጥምቀት በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት እየተከበረ ነው

የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት...