በስንዴ ዱቄት፣ በምግብ ዘይት እና በጨው ምርቶች ላይ የብሔራዊ የምግብ ማበልጸጊያ ምልክትን መጠቀም ግዴታ ተደረገ

Date:

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት በሀገሪቱ በሚመረቱ ቁልፍ የምግብ ምርቶች ላይ የብሔራዊ የበለፀገ ምግብ ምልክት (ፎርቲፋይድ) አጠቃቀም ከዚህ በኋላ አማራጭ ሳይሆን ሕጋዊ ግዴታ መሆኑን አስታወቀ።

ውሳኔው በተለይም በስንዴ ዱቄት፣ በምግብ ጨው እና በምግብ ዘይት አምራቾች ላይ ተፈጻሚ የሚሆን ሲሆን፣ ዓላማውም የኅብረተሰቡን ጤና መጠበቅና የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን መቅረፍ መሆኑ ተገልጿል።

በኢንስቲትዩቱ የስኪምና የደረጃ ምልክት አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ አቶ ኦሊያድ ሌንጮ እንደገለጹት፣ እርምጃው በምግቦች ውስጥ ለጤና ወሳኝ የሆኑ ጥቃቅን ንጥረ ነገሮች መኖራቸውን ለማረጋገጥ ያለመ ነው።

ይህም በተለይ በሕፃናት ላይ የሚከሰተውን መቀጨጭ ለመከላከልና ለነፍሰ ጡር እናቶች አስፈላጊውን የተመጣጠነ ምግብ ተደራሽ ለማድረግ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው አስረድተዋል።

ኢንስቲትዩቱ ምልክቱን ያለአግባብ በሚጠቀሙ ወይም ግዴታቸውን በማይወጡ አካላት ላይ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል። ይህንን ድንጋጌ ተላልፎ የሚገኝ ማንኛውም አካል ከአንድ እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እና/ወይም እስከ 500 ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚቀጣ ኢንስቲትዩቱ በጥብቅ አሳስቧል።

እንደ ኢንስቲትዩቱ መረጃ፣ እስካሁን ድረስ በምግብ፣ በኬሚካል፣ በኮንስትራክሽን፣ በሲቪል መሐንዲስነት እና በኤሌክትሪክ ዘርፎች የተሰማሩ 347 አምራቾች የብሔራዊ የደረጃ ምልክት የምስክር ወረቀት አግኝተው ምልክቱን በሕጋዊ መንገድ እየተጠቀሙ ይገኛሉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...