በሽምግልና ብቻ ከ135 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ዳነ

Date:

  • ​”ፍርድ ቤት መር አስማሚነት፡ ጊዜንና ገንዘብን የሚቆጥብ ዘመናዊ አሰራር”

​የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በተጠናቀቀው ግማሽ በጀት ዓመት ተግባራዊ ያደረገው “የፍርድ ቤት መር አስማሚነት” (Court-Annexed Mediation) አሰራር አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን አስታውቋል።

​የግማሽ ዓመቱ አፈጻጸም በቁጥር:

የተቋጩ መዛግብት:
በ13 ምድብ ችሎቶች 610 መዛግብት ወደ ክርክር ከመግባታቸው በፊት በስምምነት ተዘግተዋል።

የዳነ ወጪ:
በእነዚህ መዛግብት ውስጥ የነበረው የክርክር መጠን 135 ሚሊዮን 374 ሺህ ብር በላይ ሲሆን፤ ጉዳዩ በስምምነት መለቀቁ ይህን ያህል ገንዘብ እና ጊዜ ከብክነት አድኗል።

​የአሰራሩ ፋይዳ:
ይህ አሰራር ተከራካሪዎች በፍርድ ቤት የሚፈጁትን ጊዜ እና የሚያወጡትን ወጪ ከመቀነስ ባለፈ፤ ለሀገር ኢኮኖሚም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።

​ምንም እንኳን የአስማሚዎች ቁጥር ማነስ እና የተከራካሪዎች በውል ያለመቅረብ ክፍተቶች ቢኖሩም፤ አፈጻጸሙ እጅግ ተስፋ ሰጪ መሆኑ ተገልጿል።

​ሰላም እና ስምምነት ለሁሉም ይበጃል!

የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...