በቬንዙዌላው መሪ ኒኮላስ ማዱሮ ላይ የተወሰደው እርምጃ በርካታ የአለም መሪዎች አሸብሯል

Date:

በተለይ በላቲን አሜሪካ የሚገኙ ከአሜሪካ ጋር ጥሩ ግንኙነት የሌላቸው አገራት የአሜሪካን ‘ህገወጥ’ ያሉትን ዘመቻ አምርረው ተችተዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩብዮ ፕሬዝደንት ትራምፕ የተናገሩት የሚፈፅሙ ናቸው፣ ለመግለጫ እና ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ የሚናገሩ አይደሉም ሲሉ ሌሎችን ከወዲሁ የሚያሰጋ ሃሳብ ከደቂዳዎች በፊት በጋራ በተሰጠ መግለጫ ወቅት ተናግረዋል።

በርካቶች የአገራት ሉአላዊነት እና የአለም ህግ ጥያቄ ውስጥ እንደገባ እየገለፁ ሲሆን።

ከወደ ሩስያ የቀድሞው ፕሬዝደንት ዲሚትሪ ሜድቬዴሽ የኒኩሌር መሳሪያ ከሌለህ መቀለጃ ነህ ሲሉ የአለምን ፍርደ ገምድልነት እና የምእራባውያንን ለተመሳሳይ ሁነት የሚከተሉትን ሁለት አይነት አካሄድ ወርፈዋል።

አለሁልህ ሲሉ የነበሩት ቻይና እና ሩስያ ለማዱሮ መንግስት ምንም አለማድረጋቸው ‘የአህያ ባል’ እያስባላቸው ይገኛል።

አሜሪካ ዳግም የአለም ዳኛ መሆኗን አስመስክራለች ሲሉ ከወራት በፊት በኢራን ያደረሰችውን ጥቃት በማስታወስ በማህበራዊ ሚዲያ በተለይ በኤክስ አስተያየታቸውን ያጋሩም የበረከቱ ናቸው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...

ከአሜሪካ ጋር የሚኖረው “የጨዋታው ሕግ ተቀይሯል፤ የተመጣጠነ ምላሽ ዘመን አብቅቷል

ኢራን ከአሜሪካ በኩል ለሚሰነዘርባት ጥቃት የምትሰጠው ተመጣጣኝ የአጸፋ ምላሽ...

የ2.5 ቢሊየን ብር ግዙፍ ፕሮጀክት በአታ ለማርያም ገዳም በመስከረም ወር የመሠረት ድንጋይ ሊያኖር ነዉ

​በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ የታዕካ ነገሥት...

የዲቪ ዕድለኞች የማመልከቻ ሂደታቸውን እንዲቀጥሉ ተወሰነ!

የአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት በዲቪ ሎተሪ አመልካቾች የማመልከቻ ሂደት...