በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 32 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል

Date:

መንግስት የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው በፈጠረው ምቹ ሁኔታ ከሁሉም ምንጮች32 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ገለጹ።

የግሉ ዘርፍ ተዋናዮችን፣ፖሊሲ አውጪዎችንና የፋይናንስ ተቋማትን በማሳተፍ በዘላቂ ልማት፣ በማክሮ ኢኮኖሚ፣ በመዋቅራዊና በንግድ ዙሪያ የሚመክረው የኢትዮጵያ የፋይናንስ ጉባኤ የግል ዘርፍ መድረክ እየተካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በዚህ ወቅት፣ የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ እና ቀጣይነት ያለው የሀገር ዕድገትን ለማረጋገጥ የተሟላ የማክሮኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ገቢራዊ መደረጉን ገልጸዋል።

በዚህም የዋጋ ግሽበትን በግማሽ መቀነስ፣ የውጭ ምንዛሬ በገበያ እንዲወሰን በማድረግ የምንዛሬ ክምችትን ማሳደግ እንዲሁም በመሰረታዊ ዘርፎች ላይ ምርታማነትንመጨመር ተችሏል ብለዋል።

መንግስት በ2016 በጀት ዓመት ከሁሉም ምንጮች ያገኘው የውጭ ምንዛሪ ግኝት 24 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር እንደነበር አስታወሰው፥ ከተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ወዲህ በ2017 በጀትዓመት 32 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ተገኝቷል ማለታቸውን ኢዜአ
ዘግቧል።

የሀገር እድገት በመንግስት ብቻ የሚረጋገጥ አይደለም ያሉት የባንኩ ገዥ፥ የግሉ ዘርፍ የነቃ ተሳትፎና ትብብር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከባድ ሙስና የተከሰሱትን 4 ተከሳሾችን፤ ፖሊስ ፍርድ ቤት ማቅረብ ሳይችል ቀረ

በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው በፖሊስ የ'ይፈለጋሉ" ማስታወቂያ የወጣባቸው...

ስለመካከለኛው ምስራቅ አዲስ ውጥረት እስካሁን የታወቁ ጉዳዮች

🔸 ትላንት ምሽት ከኢራን ግዛት የተተኮሰ የሮኬት ጥቃት በሰሜናዊ...

የወንጀል ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕጉ በጋዜጣ እስኪታተም ረቂቅ ሰነዶችን ከመጠቀም እንዲቆጠብ የፍትሕ ሚኒስቴር አሳሰበ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፍትሕ ሚኒስቴር አዲሱ የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ...

ፔንታጎን የእስራኤል ስለላ እንደሚያሳስበው ተገለጸ

ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ፔንታጎን እስራኤል ከፍተኛ ልዑኮችን ጨምሮ የአሜሪካ...