ሀገር አቀፍ የሕግ አውጪዎች የጋራ ምክክር መድረክ ላይ ገለፃ የሰጡት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ንዋይ፥ በትግራይ ክልል ምርጫ ይደረጋል ወይ? የሚደረግ ከሆነስ ምን ያህል ዝግጅት ተደርጓል? የሚሉ ጥያቄዎችን አስተናግደዋል።
ምክትል ሰብሳቢው በምላሻቸው በክልሉ ምርጫው እንደሚደረግ አስታውቀዋል።
ጉዳዩን በተመለከተም ከክልሉ ጊዜያዊ መስተዳድርና በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፖርቲዎች ጋር ውይይት መደረጉን ስለመግለፃቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያጋራው መረጃ ይጠቁማል።
7ኛውን ጠቅላላ ሐገራዊ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለማካሄድ የታቀደ ሲሆን፥ የምርጫው ውጤት ደግሞ ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ እንደሚደረግ ይጠበቃል።
የአራዳ ኤፍ ኤም
