በአንድ ቀን 2 መኪኖች የደረሳቸው ባለትዳሮች

Date:

ኢትዮ ቴሌኮም በኢትዮ 130 ሜጋ ፕሮሞና ኢትዮ 131 ላኪ ስሎት ዕድለኛ ለሆኑ ደንበኞቹ የተለያዩ ሽልማቶችን አስረክቧል።

በዛሬው ዕለትም ሁለት ዘመናዊ የኤሌክትሪክ አውቶሞቢሎች ርክክብና የመጨረሻዎቹ ስድስት መኪኖችን ዕጣ የማውጣት ሥነ- ሥርዓት አካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ከወራት በፊት በዕጣ ያሸነፈውን ቢዋዲ መኪና ለመረከብ ከባለቤቱ ጋር ከጅማ የመጣው ሳሙኤል ጣፋ ሽልማቱን የተረከበ ሲሆን፤ በዕለቱ በተከናወነው ሌላኛው የሽልማት መርሐ ግብር ላይ ደግሞ ባለቤቱ ወይዘሮ እሌኒ ለማ የሌላ ኤሌክትሪክ መኪና ባለድል ሆናለች።

በትዳር 10 ዓመታትን ያስቆጠሩትና የ3 ልጆች ወላጅ የሆኑት አቶ ሳሙኤል ጣፋ እና ባለቤታቸው ወይዘሮ እሌኒ ለማ፤ ከኢትዮ ቴሌኮም የኤሌክትሪክ መኪናዎችን በዕጣ በመሸለም የልዩ ዕድል ባለቤት ሆነዋል።

አቶ ሳሙኤል ጣፋ ኢትዮ ቴሌኮም 130ኛ ዓመት ክብረ-በዓሉን ምክንያት በማድረግ ለደንበኞቹ ባዘጋጀው የዕድለኝነት ዕጣ መስከረም ወር ላይ ቢዋይዲ ኢቱ (BYD e2) የተሰኘች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አሸናፊ ይሆናሉ። ሽልማታቸውን ለመረከብም ባለቤታቸውን ወይዘሮ እሌኒን አስከትለው ከአሰላ ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ።

ደስታቸውን ለመካፈል በሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ሳለ ግን ዛሬ ሌላ ያልታሰበ ዕድል ወደ ቤታቸው ገባ።
በዕለቱ ለሌሎች ስድስት መኪኖች ዕጣ ሲወጣ፣ በአዳራሹ ውስጥ ተገኝተው የነበሩት ባለቤታቸው ወይዘሮ እሌኒ ለማ፤ የአይዲ ፎር (ID.4) የኤሌክትሪክ መኪና ተሸላሚ መሆናቸው እዚያው በስልክ ተደውሎ ተነገራቸው።

ወይዘሮ እሌኒ ስለ አሸናፊነታቸው ሲናገሩ፤ በድንገት ስልካቸው ሲጠራ በሁኔታው መደንገጣቸውን ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጠ/ሚ ዐቢይ ከተለያዩ የዓለም መሪዎች ጋር በCOP32 ዝግጅትና ትብብር ዙሪያ ተወያዩ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቱርክ አንታሊያ በተካሄደው COP31...

ዲጂታል ፈጣሪዎች ግብር ይከፍላሉ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፌዴራል የገቢ ግብር ደንብን ለማሻሻል ያወጣው...

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...