በኢራን ላይ የሚካሄደው ዘመቻ አላበቃም

Date:

ከኢራን ጋር የሚደረገው ጦርነት ገና አላበቃም ሲሉ የእስራኤል ጦር ዋና አዛዥ ኢያል ዛሚር ተናገሩ።

ኢራንና አጋሮቿ በእኛ እይታ ውስጥ ናቸው ሲሉ በወታደራዊ ግምገማ ስብሰባ ወቅት ተናግሯል። በኢራን ላይ የሚካሄደው ዘመቻም አላበቃምም ብለዋል።

በጋዛ የሚካሄደው ጦርነት የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ያደረገው እጅግ ውስብስብ ጦርነት መሆኑን ጠቅሰው በጦርነት ብዙ ዋጋ እየከፈልን ነው፤ ዓላማችንን ከግብ ለማድረስ መስራታችንን እንቀጥላለን ብለዋል።

ከጥቂት ወራት በፊት እስራኤል በኢራን የኒኩሊየር ተቋማት ላይ በፈፀመችው ድንገተኛ የአየር ጥቃት ሁለቱ ሀገራት ወደ ሙሉ ጦርነት መግባታቸው ይታወቃል። በጦርነቱ አሜሪካ ከእስራኤል ጎን በመሰለፍ ኢራን ላይ መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት ፈፅመለች።

የሁለቱ ሀገራት ጦርነት ከ12 ቀናት በኃላ በተኩስ አቁም ስምምነት የተቋጨ ቢሆንም ዳግም ሊቀሰቀስ የሚችልበት ዕድል እንዳለ ይነገራል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ ብር እና የደቡብ ሱዳን ፓውንድ በዓለም ላይ ደካማ አፈጻጸም ካሳዩት ተርታ ተመደቡ

 የኢትዮጵያ ብር እና የደቡብ ሱዳን ፓውንድ እ.ኤ.አ በ2025 (ከታኅሣሥ...

የኢራን ጠቅላይ መሪ የደረሰባቸው ከፍተኛ እና አካል የሚያጎድል ጉዳት እንደሆነ ተዘገበ

የኢራን ጠቅላይ መሪነት ሥልጣንን ከተረከቡ ወዲህ በአካል ያልታዩት ሞጅታባ...

ኢትዮጵያ እና ፓኪስታን የባህር ላይ የንግድ ጥምረት ለመመስረት ተስማሙ

ኢትዮጵያ እና ፓኪስታን የንግድ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ጅቡቲን የሚያካትት ባለሦስትዮሽ...

56 ዓመት ያስቆጠረው የዕውቀት በር የመጻሕፍ መሸጫ ተመሰገነ

ለባዊ ዓለም አቀፍ አካዳሚ " ትውልድን በስነ ጽሑፍ ማስተሳሰር...