በኢራን በተቀሰቀሰው ተቃውሞ የሟቾች ቁጥር ከ500 በላይ መድረሱን ተገለፀ

Date:

በኢራን በተቀሰቀሰው ተቃውሞ 490 ተቃዋሚዎች እና 48 የጸጥታ ኃይሎች መሞታቸውን በአሜሪካ የሚገኝ አንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን እሁድ ዕለት አስታወቀ።

በሌላ በኩል ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለተቃዋሚዎች ድጋፍ ለመስጠት ጣልቃ ለመግባት ያሰሙትን ማስጠንቀቂያ ተግባራዊ የሚያደርጉ ከሆነ፣ ቴህራን የአሜሪካን የጦር ሰፈሮች ኢላማ እንደምታደርግ ዝታለች።

የኢስላማዊ ሪፐብሊክ ኃይማኖታዊው አስተዳደር ከጎርጎሮሳውያኑ 2022 ወዲህ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ እያጋጠመው ይገኛል። ትራምፕ በበኩላቸው በተቃዋሚዎች ላይ የኃይል እርምጃ የሚወሰድ ከሆነ ጣልቃ እንደሚገቡ በተደጋጋሚ አስጠንቅቀዋል።

መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ህራና (HRANA) በኢራን ውስጥና ከውጭ ካሉ አክቲቪስቶች አገኘሁት ባለው ወቅታዊ መረጃ መሠረት፤ በሁለት ሳምንታት ተቃውሞ የ490 ተቃዋሚዎች እና የ48 የጸጥታ ኃይሎች ሞት መመዝገቡን ገልጿል። በተጨማሪም ከ10,600 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን ድርጅቱ ገልጿል ሲል ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

ኢራን እስካሁን ይፋዊ የሟቾች ቁጥር ያልገለጸች ሲሆን፤ ሮይተርስም የቀረቡትን አሃዞች በተናጥል አጣርቶ ለማረጋገጥ አልቻለም።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ጉዳይ ያሉ አማራጮችን ለመወያየት ማክሰኞ ዕለት ከከፍተኛ አማካሪዎቻቸው ጋር እንደሚገናኙ አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን እሁድ ዕለት ለሮይተርስ ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...