በኢትዮጵያ በሚሊየን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ላይ የሉም

Date:

በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በተፈጠረ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ያለባቸው ተማሪዎች ሳይሄዱ ቀርተዋል፡፡

ባለፉት አመታት በነበረ አሁንም ድረስ በአንዳንድ አካባቢዎች በቀጠለ የሰላም እጦት ትምህርት ቤቶች በሙሉም ሆነ በከፊል ተጎድተዋል፤ ሰዎች ሰላምን ፍለጋ ቀያቸውን ለቀው ወጥተዋል፡፡

በነዚህ እና በሌሎች ምክንያች ልጆች ከትምህርት ገበታቸው እርቀዋል፡፡

እንደማሳያም የሰላም እጦት ከነበሩባቸው እና አሁንም ድረስ ችግሩ ከቀጠሉባቸው አካባቢዎች መካከል የሆነው አማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን ከጀመረ ወራት ማስቆጠሩ ቢታወቅም እመዘግባለው ብሎ ካቀደው ተማሪ 3 ሚሊየኑን እንዳላገኘ ተናግሯል፡፡

በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት አመታት በተፈጠረ ሰላም እጦት ምክንያት በሚሊየን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እርቀው ከርመዋል፡፡

በዚህ ምክንያት ተማሪዎቹ በተከታታይ ሁለት አመት፤ ሶስት አመት እና ከዚያ በላይ ለሚሆን ጊዜ ከመፀሀፍ እና ደብተር እርቀው የቆዩ መኖራቸውን ከክልሎቹ ሰምተናል፡፡

ትውልድን ለማዳን ካስፈለገ ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎችን ወደ ገበታቸው እንዲመለሱ ማድረግ ላይ በትኩረት መስራት ይኖርብናል ተብሏል። ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ እና የቻይና አየር መንገዶች የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ቻይና ሳውዘርን አየር መንገድ በቻይና...

ሁቲዎች በሳዑዲ የነዳጅ ኩባንያ አስተዳደር ሕንጻ ላይ በፈጸሙት ጥቃት በእሳት ተያያዘ

የሳዑዲ አረቢያ የኢነርጂ ሚኒስቴር በአገሪቱ ምሥራቃዊ ግዛት የሚገኘው ከዓለም...

የሹመት ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  ሹመት የሰጧቸው አመራሮች፡- 1. አቶ...

እንደዚህ ዓይነቱ ብልሹ ኣሰራርን ካላረምን በቀር መልካም ኣስተዳደርን …

በኣጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኣጠቃላይ...