በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መሐል ችግር የፈጠረዉ የቀይ ባህር ጥያቄ አለመሆኑን ተናገሩ

Date:

አንዳንድ ሰዎች በኢትዮጵያና በኤርትራ መሀከል ችግር የተፈጠረዉ የኢትዮጵያ መንግስት የቀይ ባህር ጥያቄ ስላነሳ ነዉ የሚሉ ወሬዎች መኖራቸዉን አንስተዉ እዉነታዉ ግን ይህ አይደለም ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ችግር በትግራይ ጦርነት ወቅት የተጠነሰሰ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ግጭቱ በትግራይ ጦርነት ወቅት ከኤርትራ ጦር ዘረፋ እና ግድያ ጋር ተያይዞ የተጀመረ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናግረዋል፡፡

በአድዋ ከተማ ፋብሪካ ሲዘርዱ እንደነበርና አዲግራትም በተመሳሳይ ይህን ድርጊት ሲፈጸም እንደነበረ አንስተዉ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በሰዓቱ በሁለቱም በኩል መዋጋት እንዳልቻለ ተናግረዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እያካሄ ነዉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስትን የ2018 በጀት ዓመት በ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በሚያቀርቡ ወቅት ነዉ ይህን ያሉት።

ይህንን ችግር ለመፍታት የተለያዩ የመንግስት አካላት ኤርትራ ሄደዉ እንደነበረና ምንም መፍትሄ ግን እንዳላመጡ ገልፀዋል።

የቀድሞዎቹን የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ደመቀ መኮንን እና ገዱ አንዳርጋቸውን ወደ ኤርትራ ልከው ሕዝቡን እንዳያጎሳቁሉ መጠየቃቸውንም ለፓርላማዉ ተናግረዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...

ከአሜሪካ ጋር የሚኖረው “የጨዋታው ሕግ ተቀይሯል፤ የተመጣጠነ ምላሽ ዘመን አብቅቷል

ኢራን ከአሜሪካ በኩል ለሚሰነዘርባት ጥቃት የምትሰጠው ተመጣጣኝ የአጸፋ ምላሽ...

የ2.5 ቢሊየን ብር ግዙፍ ፕሮጀክት በአታ ለማርያም ገዳም በመስከረም ወር የመሠረት ድንጋይ ሊያኖር ነዉ

​በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ የታዕካ ነገሥት...

የዲቪ ዕድለኞች የማመልከቻ ሂደታቸውን እንዲቀጥሉ ተወሰነ!

የአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት በዲቪ ሎተሪ አመልካቾች የማመልከቻ ሂደት...