በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ ቀነሰ

Date:

​የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቬንዙዌላ ከ30 እስከ 50 ሚሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ለአሜሪካ እንደምታቀርብ ማስታወቃቸውን ተከትሎ፣ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ከአንድ በመቶ በላይ መቀነሱን ዘ ጋርዲያን ረቡዕ ዕለት ዘግቧል።

​ዓለም አቀፍ መለኪያ የሆነው የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ረቡዕ ዕለት ከአንድ በርሜል ከ60 ዶላር በታች የወረደ ሲሆን፣ የአሜሪካ ድፍድፍ ነዳጅ ደግሞ በ1.4 በመቶ ቀንሶ 56.44 ዶላር ሆኗል።

​የአሜሪካው ጣልቃ ገብነት ቬንዙዌላ ወደ ቻይና የምታደርገው የነዳጅ ኤክስፖርት ሊያቋርጥ ይችላል የሚል ስጋትንም ፈጥሯል።

ይህች የላቲን አሜሪካ ሀገር ከምታመርተው ድፍድፍ ነዳጅ ውስጥ 80 በመቶ የሚሆነውን ወደ ቻይና ትልካለች። ይህም ቤጂንግ ለድፍድፍ ነዳጅ ከፍተኛ ዋጋ እንድትከፍል ሊያስገድዳትና ከዋይት ሀውስ ጋር ያለውን ውጥረት ሊያባብሰው ይችላል።

​የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ረቡዕ ዕለት በሰጠው መግለጫ ቬንዙዌላ “በተፈጥሮ ሀብቷና በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎቿ ላይ ሙሉ እና ቋሚ ሉዓላዊነት አላት” ብሏል።

አክሎም አሜሪካ ነዳጁ ለሷ እንዲሰጥ ያቀረበችው ጥያቄ “ዓለም አቀፍ ሕግን የሚጥስ፣ የቬንዙዌላን ሉዓላዊነት የሚጋፋ እና የቬንዙዌላን ሕዝብ መብት የሚጎዳ ነው” ሲል ገልጿል።

​ቀደም ብሎ ትራምፕ “ትሩዝ ሶሻል”  በተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፦ “እንደ አሜሪካ ፕሬዝዳንትነቴ ይህ ገንዘብ ለቬንዙዌላ እና ለአሜሪካ ሕዝቦች ጥቅም እንዲውል እቆጣጠረዋለሁ… ይህ ነዳጅ በመርከብ ተጭኖ በቀጥታ በአሜሪካ ወደሚገኙ የመጫኛ ወደቦች ይመጣል” ብለው ነበር።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...

ከአሜሪካ ጋር የሚኖረው “የጨዋታው ሕግ ተቀይሯል፤ የተመጣጠነ ምላሽ ዘመን አብቅቷል

ኢራን ከአሜሪካ በኩል ለሚሰነዘርባት ጥቃት የምትሰጠው ተመጣጣኝ የአጸፋ ምላሽ...

የ2.5 ቢሊየን ብር ግዙፍ ፕሮጀክት በአታ ለማርያም ገዳም በመስከረም ወር የመሠረት ድንጋይ ሊያኖር ነዉ

​በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ የታዕካ ነገሥት...

የዲቪ ዕድለኞች የማመልከቻ ሂደታቸውን እንዲቀጥሉ ተወሰነ!

የአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት በዲቪ ሎተሪ አመልካቾች የማመልከቻ ሂደት...