Home ልዩ ልዩ ዜና በደብረጺዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን ትላንት ማምሻውን መግለጫ ሰጥቷል

በደብረጺዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን ትላንት ማምሻውን መግለጫ ሰጥቷል

በደብረጺዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን ትላንት ማምሻውን መግለጫ ሰጥቷል

በመግለጬውም ትግራይ ላይ ሽብር እንደታወጀ፣ ግጭት እንደተጀመረ የሚነዛው ሀሰት ነው። ትግራይ ሰላም ነች። የተደረገው በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት የትግራይን ጉዳይ በአግባቡ ያልያዘውን የጊዜያዊ መስተዳድር ፅህፈትቤቶች ለህዝብ አግ ግሎት እንዲሰጡ በማድረግ ሰላምና መረጋጋት ለትግራይ ማምጣት ነው።

ጊዜያዊ መስተዳደሩ 50 ሲደመር አንድ የተወከለበትን ህወሓት ፍላጎት ተግባራዊ እንዲሆን አልሰራም። ጭራሽ የትግራይ ፀጥታ ሀይላትን ከሀላፊነታቸው አንስቷል። ይህ ደግሞ ተቀባይነት የለውም።

ለፌደራም ሆነ ለአለማቀፍ ማህበረሰብ የምናሳስበው እኛ የፕሪቶሪያ ስምምነት እንዲተገበር፣ የትግራይ ህዝብ አጠቃላይ መሻት እንዲሳካ ነው የምንፈልገው እንጂ ሌላ ዙር ግጭት በትግራይ እንዲነሳ አይደለም። ተፈናቃዮች ይመለሱ። የፕሪቶሪያ ስምምነት ይፈፀም ነው የኛ ጥያቄ። ይህ ደግሞ የትግራይ ህዝብ ጥያቄ ነው።

ከኤርትራ ጋር ግኑኝነት እንዳደረግን የሚነዛው ወሬ ሀሰት ነው። እርግጥ ለትግራይ ሰላም ሲባል ከአማራም ከሱዳንም ከአፋርም ከኤርትራም ጋር በሰላም ተቀራርበን ችግርን ብነፈታ ምንም ችግር የለውም። አንዳንዶች እንደሚሉት ድጋፍ ለማግኘት የተገናኘነው የውጭ አካል ግን የለም።

የቀድሞ ጓዶቻችን በአዲሳባ ዛሬ የሰጡትን መግለጫ አይተነዋል። የፌደራል መንግስት እንዲገባ ጥያቄ ማቅረባቸው አሳዝኖናል። እኛ ከፌደራል መንግስት ጋር በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ችግር ለመፍታት ዝግጁ ሆነን ሳለ እንዲህ አይነት ጥሪ ማድረግ ልክ አይደለም።

ለሀገራችን ማህበረሰብ፣ በቅርቡ ለተረበሸ ህዝባችን በሙሉ ትግራይ ሰላም መሆኗን። የተረጋጋች መሆኗን ልንገልፅ እንፈልጋለን።