በጎንደር ከተማ በሚከበረው የጥምቀት በዓል ከ2 ሚሊዮን በላይ ጎብኝዎች ይጠበቃሉ

Date:

በጎንደር ከተማ በ2018 ዓ.ም በሚከበረው የጥምቀት በዓል ከ2 ሚሊዮን በላይ ጎብኝዎች እንደሚጠበቁ የከተማዋ የቅርስ ጥበቃ ተቋም ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።

ከጥር 2 እስከ ጥር 10 ቀን 2018 ዓ.ም በከተማዋ የተለያዩ አውደ ርዕዮች መዘጋጀታቸውን የገለጹት የጎንደር ዓለም አቀፍ የቅርስ አስተዳደር መሪ አቶ ጌታሁን ስዩም፤ በዓሉን ለማክበር ከ2 ሚሊዮን በላይ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ጎብኝዎች እንደሚጠበቁ ተናግረዋል።

ክብረ በዓሉ “ኢትዮጵያን በጎንደር” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር የጠቀሱት አቶ ጌታሁን፤ ለሀገራቸው መስዋዕትነት የከፈሉ ኢትዮጵያውያን የሚመሰገኑበት ልዩ መድረክ መዘጋጀቱንም ገልጸዋል።

በከተማዋ ወደ 15 የሚጠጉ ባለኮከብ ሆቴሎች መኖራቸውን ያነሱት መሪው፤ ከ200 በላይ በኮከብ ደረጃ ያልተቀመጡ ሆቴሎችም እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል። ሆቴሎቹ እንግዶችን በመደበኛ ዋጋ እንዲያስተናግዱ ውሳኔ መተላለፉንም አክለዋል።

በከተማዋ ምንም ዓይነት የፀጥታ ስጋት አለመኖሩን የገለጹት አቶ ጌታሁን፤ ለጎብኝዎች ደህንነት የከተማዋ ፖሊስ ሙሉ ኃላፊነት መውሰዱን ጠቁመዋል። በዓሉን ምክንያት በማድረግ ወደ ከተማዋ ይገባሉ ተብለው የሚጠበቁ እንግዶች ቁጥር ከሆቴሎች የመኝታ አቅም ጋር የማይመጣጠን በመሆኑ “አንድ እንግዳ ለአንድ ቤተሰብ” የሚል አሰራር መዘርጋቱንም አስታውቀዋል።

የእንግዶችን የቆይታ ጊዜ ለማራዘም የተለያዩ ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውንና ለዚህም የዘርፉ ባለሙያዎች በሥራ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

በተያያዘ መረጃ በአማራ ክልል ከታህሳስ 28 እስከ ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም በሚከበሩ ክብረ በዓላት ላይ ከ3 ሚሊዮን በላይ ጎብኝዎች እንደሚጠበቁ የክልሉ ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ማስታወቁ ይታወሳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...