በ2017 ዓመት ከ285 ሺህ በላይ የእንስሳት እርድን ቢያከናውንም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ11 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል

Date:

የ2017 በጀት ዓመት ክንውንን አስመልክቶ የተቋሙ የእርድ አገልግሎትና የስጋ ስርጭት ዳይሬክቶሬት እቅድ አፈፃፀምን ገምግሟል።

በበጀት አመቱ ድርጅቱ 323ሺህ 29 የእንስሳት እርድን ለማከናወን አቅዶ የነበረ ቢሆንም 285 ሺህ 451 የእንስሳት እርድን ስለማከናወኑ አስታውቋል።በዚህም የእቅዱን 88 በመቶ ማሳካት መቻሉ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

በበጀት ዓመቱ 198 ሺህ 745 የዳልጋ ከብት ለማረድ ታቅዶ እንደነበር የገለፀው ድርጅቱ 166ሺህ 916 እርድ ማከናወኑን ተናግሯል።ይህም የእቅዱን 84 በመቶ አፈፃፀም ማሳካቱን ሪፖርቱ ያሳያል፡፡

በተጨማሪም 124 ሺህ 284 ትናንሽ እንስሳት ማለትም በግና ፍየልን ለማረድ ታቅዶ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን 118ሺህ 541 የእንስሳት እርድን በማከናወን የእቅዱን 95 በመቶ ማከናወን መቻሉን ሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡በጥቅሉ በ2017 በጀት አመት 285 ሺህ 451 የእንስሳት እርድ መከናወኑ በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ የእርድ መጠኑ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ11 በመቶ ቅናሽ ያሳየ ስለመሆኑ ድርጅቱ በማህበራዊ ድህረ ገጹ ላይ አጋርቷል።ለዚህም ዋነኛ ምክንያቱ በየአካባቢው የሚታረደው ህገ ወጥ እንስሳት መበራከት መሆኑ ተጠቁሟል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አዲስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ኢራን የበለጠ ምላሽ በመስጠት የተራዘመ ጦርነት እንደምታካሂድ አስታወቀች

ከፍተኛ የኢራን ወታደራዊ ባለሥልጣናት አሜሪካ ሌላ ዙር ጥቃት በአገራቸው...

ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በሥራ ቡድን ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘውን...

የጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ 28 የውጭ ዜጋ ተማሪዎችን ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ጋር ማስተሳሰሩን ገለጸ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ መርሃ-ግብር አማካኝነት በዘንድሮው ዓመት...

የሕግ ተማሪዎቹ አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፍ የምስለ-ችሎት ፍጻሜ አለፉ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በአህጉራዊው የዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት...