በ31ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የማንቹርያን ደርቢ ይጠበቃል

Date:

በ31ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሀ ግብር በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ሲደረጉ ማንችስተር ዩናይትድ ከማንችስተር ሲቲ የሚያደርጉት የማንቹርያን ደርቢ ተጠባቂ ሆኗል፡፡

31ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከነገ ጀምረው ሲካሄዱ ነገ 8፡30 ላይ በጉዲሰን ፓርክ ኤቨርተን ከአርሰናል በሚያደርጉት ግጥሚያ ጅማሮውን ያደረጋል፡፡

ብራዚላዊውን ተከላካይ ጋብርኤል ማጋሀሌስን እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ በጉዳት ያጡት መድፈኞቹ በቶፊሶቹ ሊፈተኑ እንደሚችሉ ሲጠበቅ በሳምንቱ አጋማሽ በፉልሀም ላይ ያስመዘገቡትን ድል ለመድገም ይፋለማሉ፡፡

እሁድ የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ፉልሀምን ከሜዳው ውጭ ወደ ክራቨን ኮቴጅ አቅንቶ 10፡00 ላይ ሲገጥም ብራዚላዊው ወሳኙ ግብ ጠባቂ አሊሰን ቤከር ወደ ቋሚ 11 እንደሚመለስ ይጠበቃል፡፡

ቀያዮቹ ከፊታቸው የሚጠብቋቸውን 4 ጨዋታዎች ማሸነፍ ከቻሉ ሻምፒዮን መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡

በተመሳሳይ ሰአት በሳምንቱ አጋማሽ ቶተንሃምን በመርታት 4ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ቼልሲ ወደ ጂቴክ ኮምዩኒቲ ስታድየም አቅንቶ ለታላላቅ ክለቦች ፈታኝ የሆነው ብሬንትፎርድን ይገጥማል፡፡

ምሽት 12፡30 ላይ የሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ ኦልድትራፎርድ ላይ ሲደረግ በማንቹርያን ደርቢ ማንችስተር ዩናይትድ የከተማ ተቀናቃኙ ማንችስተር ሲቲን ያስተናግዳል፡፡

በቁርጭምጭሚት ጉዳት ለ7 ሳምንታት ያህል ከሜዳ የራቀው ኖርዌያዊው የማንችስተር ሲቲ አጥቂ አርሊንግ ሀላንድ ከጨዋታው ውጭ መሆኑን አስቀድሞ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ማንችስተር ዩናይትድ ለጨወታው የትኬት ዋጋ ቅናሽ ማድረጋቸውን ተዘግቧል፡፡

ሀገሬ ቲቪ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫ በሚያካሂድባቸው ቦታዎች ሁሉ እሳተፋለሁ

በዘንድሮው ሀገራዊ ምርጫ እንደሚሳተፍ ያስታወቀው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትህ...

በሲዳማ ክልል ከ62% በመቶ በላይ የሚታረሰው መሬት በአሲዳማነት የተጎዳ ነዉ

በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ የሚታየው የምርታማነት ማነቆ በዋናነት የመሬት አሲዳማነት...

የኢትዮጵያ እዳ እና ሃብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎች ስብሰባ ሳይገኙ ቀሩ

የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ እዳ እና...

የኢትዮጵያ እና ሕንድ የቆየ ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት

የኢትዮጵያ እና ሕንድ የቆየ ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት የአፍሪካ-ሕንድ...