ምርጫ ቦርድ በትግራይ ክልል ለሚካሄደው ምርጫ ዝግጅት እንዲደረግ አሳሰበ

Date:

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በ2018 ዓ.ም ለሚያካሂደው 7ኛው ዙር አገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

ቦርዱ ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በጻፈው ደብዳቤ፣ በክልሉ የሚገኙ የምርጫ ጣቢያ ጽሕፈት ቤቶች ዝግጁ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል።

​ዋና ዋና ነጥቦች፦

📌​የምርጫ ቀን፦ 7ኛው አገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም እንዲካሄድ ታቅዷል።

📌​የመራጮች ምዝገባ፦ የመራጮች ምዝገባ ከየካቲት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚከናወን ተገልጿል።

📌​የተሰጠ የጊዜ ገደብ፦ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የምርጫ ጣቢያ ጽሕፈት ቤቶች አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቆ እስከ ጥር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለቦርዱ እንዲሳወቅ ጥያቄ ቀርቧል።

​ቦርዱ ቀደም ሲል በታህሳስ 03 ቀን 2018 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ የምርጫ ክልል እና የምርጫ ጣቢያ ጽሕፈት ቤቶች እንዲዘጋጁ መጠየቁን በማስታወስ፣ አሁን ላይ ስራው ተጠናቆ ሪፖርት እንዲደረግለት አሳስቧል።

​ኢትዮጵያ ምርጫ2018 ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ትግራይ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት ገለጸች

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት የአገሪቱ...

ከትግራይ ዩኒቨርሲቲ ታጣቂዎች ካልወጡ ተማሪ አንመድብም

ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል የሚገኙ መቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና...

ኢራን አሜሪካ የጣለችባት ዕገዳ የበለጠ የሚጎዳው ዋሽንግተንን ነው አለች

አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው የኢኮኖሚ እና የባሕር እንቅስቃሴ እገዳ...

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...