ተጫራቾች አማካይ የመግዣ ዋጋ 154.92 ብር በዶላር ሆኖ ተመዝግቧል

Date:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጥር 12 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው 15ተኛዉ ዙር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ፣ ከንግድ ባንኮች የቀረበው የዶላር ፍላጎት ባንኩ ለሽያጭ ካቀረበው መጠን በላይ መሆኑን አስታውቋል።

ባንኩ በዚህኛው ዙር ጨረታው 70 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያቀረበ ቢሆንም፣ በጨረታው ላይ የተሳተፉ 21 የንግድ ባንኮች በድምሩ 94.7 ሚሊዮን ዶላር ለመግዛት ፍላጎት ማሳየታቸውን ገልጿል።

ይህም በገበያው ውስጥ ያለውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት አመላካች ሆኖ ተመዝግቧል።

በጨረታው ሂደት ላይ የተሳተፉት 15 ባንኮች ባቀረቡት የመግዣ ዋጋ መሠረት አሸናፊ መሆናቸው የታወቀ ሲሆን፣ በዚህም መሠረት የተሳካላቸው ተጫራቾች አማካይ የመግዣ ዋጋ 154.92 ብር በዶላር ሆኖ ተመዝግቧል።

በተጨማሪም የጨረታው ዝቅተኛ ተቀባይነት ያገኘ ዋጋ ወይም የመዝጊያ ዋጋ 154.7800 ብር መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ በጨረታው ወቅት ከፍተኛው የቀረበ ዋጋ 155 ብር እና ዝቅተኛው ደግሞ 153 ብር ሆኖ ማለፉን ባንኩ በዝርዝር አስታውቋል።

ይህ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ብሔራዊ ባንክ በየሁለት ሳምንቱ ለማካሄድ ባወጣው መርሃ-ግብር መሠረት የተከናወነ ሲሆን፣ ቀጣዩ ጨረታም በተመሳሳይ ሁኔታ ከሁለት ሳምንት በኋላ እንደሚከናወን ባንኩ አረጋግጧል።

ይህ በየጊዜው የሚደረግ የዶላር ሽያጭ በንግድ ባንኮች ዘንድ ያለውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመቅረፍ፣ የኤክስፖርት እና የኢምፖርት ዘርፉን ለማገዝ እንዲሁም አጠቃላይ የውጭ ምንዛሪ ገበያው በራሱ ፍላጎትና አቅርቦት ላይ ተመስርቶ እንዲረጋጋ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ይታወቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ትራምፕ የኢራን የኒውክሌር ተቋም ላይ ጥቃት ለማድረስ ዛቱ

አሜሪካ በኢራን ላይ የምታደርሰው ጥቃት 11ኛ ቀኑን ይዟል። ፕሬዝዳንት...

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአሜሪካ ” American Space ” ማዕከል ተመረቀ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቨን ማሲንጋ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተቋቋመውን "American...

አሐዱ ባንክ ለ 8ኛ ጊዜ የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናወነ

አሐዱ ባንክ ሥራ የጀመረበትን 4ኛ ዓመት በማስመልከት የተለያዩ ኩነቶችን...

ዕንባ ጠባቂ ከቀረቡለት አቤቱታዎች 84% በመንግስታዊ ተቋማት ላይ የቀረቡ ናቸው

የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በተጠናቀቀው የ2018 በጅት ዓመት...