ታላቅ የሲንፎኒ ኦኬስትር ኮንሰርት ቀረበ

Date:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር 70ኛ ዓመትን እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት ምሥረታ የአልማዝ ኢዩቤልዩ በዓልን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የስትሪንግ ኦርኬስትራ በጋራ ታላቅ ሲነፎኒ ኦኬስትራ ኮንሰርት አቀረቡ፡፡

ሲንፎኒ ስትሪንግ ኦኬስትራው ካቀረበው ኮንሰርት ውስጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ኮንዳክተር ሰለሞን ሉሉ፤” እረኛው ባለዋሽንት” (ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ ፡አክሊሉ ዘውዴ) ‹‹የልቤ ጉዞ›› ኮንዳክተር (አማኑኤል ቡሌ ፤ረዳት ፕሮፌሰር አክሊሉ ዘውዴ) የአስቴር አወቀ ‹‹ጠይም ዘለግ ያለ›› ‹‹ የክቡር ዶ/ር የጥላሁን ገሠሠ ‹‹እንኳን ቆሜ ብቀበርም..›› ኮንዳክተር ዶ/ር ዕዝራ አባተ ‹‹የተነቃቃ ስሜት›› በረዳት ፕሮፌሰር አክሊሉ ዘውዴ የተቀመሩ ሥራዎች የቀረቡ ሲሆን የዕለቱን ሲነፎኒ ኦኬስትራ ኮንሰርት በ ረ/ፕ አክሊሉ ዘውዴ መራሒ ሙዚቃ መሪነት ቀርቧል፡፡
                                
በዕለቱ የሙዚቃ ተመራማሪና ባለሞያ የኢትዮጵያ ቤተመጽሐፍትና ቤተመዛግብት አገልግሎት ዋና ዳይሬክትር አቶ ሰርጸፍሬ ስብሀት እና ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ የሙዚቃ አፍቃሪያን ተገኝተዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...

ከአሜሪካ ጋር የሚኖረው “የጨዋታው ሕግ ተቀይሯል፤ የተመጣጠነ ምላሽ ዘመን አብቅቷል

ኢራን ከአሜሪካ በኩል ለሚሰነዘርባት ጥቃት የምትሰጠው ተመጣጣኝ የአጸፋ ምላሽ...

የ2.5 ቢሊየን ብር ግዙፍ ፕሮጀክት በአታ ለማርያም ገዳም በመስከረም ወር የመሠረት ድንጋይ ሊያኖር ነዉ

​በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ የታዕካ ነገሥት...

የዲቪ ዕድለኞች የማመልከቻ ሂደታቸውን እንዲቀጥሉ ተወሰነ!

የአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት በዲቪ ሎተሪ አመልካቾች የማመልከቻ ሂደት...