የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከጋቦን፣ ጊኒ ቢሳው፣ ላይቤሪያ፣ ሞሪታኒያ እና ሴኔጋል መሪዎች ጋር በንግድ ግንኙነት ላይ ለመወያየት በዋይት ሀውስ መገናኘታቸው ተዘግቧል
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአምስት የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት መሪዎችን በዋይት ሀውስ ማስተናገዳቸው ተገልጻል፡፡
ይህም አሜሪካ በአፍሪካ እየጨመረ ያለውን የጂኦፖለቲካዊ ፉክክር በመቀላቀል የንግድ ግንኙነቷን ለማጠናከር ፍላጎት አላት ተብሏል፡፡
አሜሪካ ከአፍሪካ ጋር እንደ አዲስ ግንኙነቷን በጀመረችበት በአሁኑ ወቅት ከጋቦን፣ ጊኒ ቢሳው፣ ላይቤሪያ፣ ሞሪታኒያ እና ሴኔጋል የተውጣጡ ሀገራት መሪዎች ጋር ጉባኤ ውይይት አድርጋለች፡፡
ባለፈው ወር መገባደጃ ላይ አሜሪካ በዲሞክራቲክ ኮንጎ እና በሩዋንዳ መካከል የሰላም ስምምነት እንዲኖር አስተባብራለች፡፡የዚህ አላማው አሜሪካ በሃገራቱ
ኢንቨስትመንቱዋን ለማስፋፋት መንገድ ለመክፈት እንደሆነ አናዶሉ ዘግቧል፡፡
አፍሪካ በዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በአጋርነት ከመስራት ጋር ተያይዞ ዝቅ ያለ ግምት ቢሰጣትም በተፈጥሮ ሃብቶች ከበለጸጉት አምስቱ ሃገራት ጋር የተደረገው ጉባኤ የአሜሪካ ኩባንያዎች ወደ ሃገራቱ ሄደው ኢንቨስት እንዲደርጉ ለማስቻል ነው ተብሏል፡፡
