የቬንዙዌላዋ የኒኮላስ ማዱሮ አስተዳደር ተቺና ተቃዋሚ የኖቤል ስላም ሽልማታቸውን ለፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰጡ።
ማሪያ ኮሪና ማቻዶ “ትራምፕ ለነፃነታችን የተለየ ዋጋ በመክፈላቸው የተከበረውን የኖቤል ሰላም ሽልማት ሰጥቻቸዋለሁ” ሲሉ ምክንያታቸውን አስቀምጠዋል።
የኖቤል ሽልማት ኮሚቴን አሰራር የጣሰ ነው ቢባልም ትራምፕ ሽልማቱ ተበርክቶላቸዋል።
ሽልማቱ ለሌላ አካል ተላልፎ እንደማይሰጥም ኮሚቴው ቀድሞ ማሳሰቡ የሚዘነጋ አይደለም።
ማቻዶ ፕሬዚዳንት ትራምፕን ካገኙ በኋላ በካፒቶል ለጋዜጠኞች ሀሳብ የሰጡ ሲሆን ለካራካስ ነፃነት ሪፐብሊካኑ ዋጋ ከፍለዋል ብለዋል።
በዕርግጥ ትራምፕ በካሪቢያን በኩል የቬንዙዌላን ነዳጃ ወደ አሜሪካ ለማጋዝ ያደረጉት ነው በሚል ይወቀሳሉ።
የኖቤል ሽልማት ከተሰጠ በኋላ ለማንም አሳልፎ መስጠትም ሆነ ማጋራት እንደማይቻል ግልፅ በሆነ መንገድ ቢቀመጥም ማቻዶ አሰራሩን ጥሰው ለትራምፕ ዕውቅና ሰተዋቸዋል።
ማቻዶ የኖቤል ሽልማትን ያገኙት ቬንዙዌላን ከአምባገነናዊ ወደ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ለማሻገር ባደረጉት ጥረትና ለነፃነት በከፈሉት ዋጋ ነበር ተብሏል።
ዘ ዋሽንግተን ፖስት
