ትራምፕ የኢራን የኒውክሌር ተቋም ላይ ጥቃት ለማድረስ ዛቱ

Date:

አሜሪካ በኢራን ላይ የምታደርሰው ጥቃት 11ኛ ቀኑን ይዟል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከመሬት በታች የተገነባው የቴህራን የኒውክሌር ተቋም ላይ ጥቃት እንደሚሰነዝሩ ዝተዋል።

ትራምፕ በኢራን፣ ናታንዝ የሚገኘውን ከምድር በታች የተገነባ የኒውክሌር ተቋም እንደሚመቱ መዛታቸውን ተከትሎ ቴህራን የአጸፋ ምላሽ እንደምትሰጥ አስጠንቅቃለች።

የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) እንዳለው በኢራን ላይ እየደረሰ ያለው ተከታታይ ጥቃት ዓላማው በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ “ለንግድ መርከቦች አስጊ የሆን አቅሟን ለማካደም” ነው።

የኢራን ብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገበው በቴህራን የአየር መቃወሚያዎች ሥራ እንዲጀምሩ ተደርጓል።

በታባሪዝ፣ ቻባሀር፣ ኮናርክ እና ቡሸህር ፍንዳታዎች መሰማታቸው ተዘግቧል። ቡሸህር የኢራን ብቸኛው የኒውክሌር ማብላያ ተቋም የሚገኝነት ነው።

ኢራን አሜሪካ ላደረሰችባት ጥቃት በምላሹ በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ የጦር ሰፈሮቿ ላይ ድብደባ አድርሳለች።

ኢራን እና አሜሪካ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደርሰው የነበረ ቢሆንም በሆርሙዝ ወሽመጥ አስተዳደር ጉዳይ ዳግመኛ ወደ ውጊያ ተመልሰዋል።

ኢራን “ከ30 በላይ የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት አድርሳለች” ሲል የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ከስሷል።

የኢራን ወታደራዊ ተቋማት፣ የባሕር ኃይል፣ የአየር ኃይል እና ሌሎችም የአገሪቱ የጦር መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት መፈጸሙንም አስታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አዲስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ኢራን የበለጠ ምላሽ በመስጠት የተራዘመ ጦርነት እንደምታካሂድ አስታወቀች

ከፍተኛ የኢራን ወታደራዊ ባለሥልጣናት አሜሪካ ሌላ ዙር ጥቃት በአገራቸው...

ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በሥራ ቡድን ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘውን...

የጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ 28 የውጭ ዜጋ ተማሪዎችን ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ጋር ማስተሳሰሩን ገለጸ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ መርሃ-ግብር አማካኝነት በዘንድሮው ዓመት...

የሕግ ተማሪዎቹ አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፍ የምስለ-ችሎት ፍጻሜ አለፉ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በአህጉራዊው የዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት...