ትራምፕ የፕሬዝዳንትነቱን መንበር ትተው ወደ አቅራቢነት ሊመለሱ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጡ

Date:

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ ባደረጉት የ “Truth Social” ማህበራዊ ሚዲያ ፅሁፍ፣ የፕሬዝዳንትነት ስልጣናቸውን በመተው የሙሉ ጊዜ የዝግጅት አቅራቢነትን (Host) ሙያ ለመጀመር እያሰቡ መሆኑን በጨዋታ መልክ ገለጹ።

ይህ የ79 ዓመቱ ሪፐብሊካን መሪ አስተያየት የመጣው፣ በስማቸው ወደ ተቀየረው “ትራምፕ ኬኔዲ ሴንተር” (Trump Kennedy Center) በማምራት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ ተቀምጦ ያለ ፕሬዝዳንት የክብር ሽልማት ስነ-ስርዓቱን እንዲያቀርብ የተደረገውን ስምምነት ተከትሎ ነው።

ፕሬዝዳንቱ ለተከታዮቻቸው ባቀረቡት ጥያቄ፣ በስነ-ስርዓቱ ላይ የሚያሳዩትን የ “Master of Ceremony” ወይም የመድረክ መሪነት ብቃታቸውን እንዲመዝኑላቸውና ውጤቱ ጥሩ ከሆነ “ስራዬን ትቼ ወደ ሙሉ ጊዜ አቅራቢነት ልመለስን?” ሲሉ ጠይቀዋል።

ትናንት ምሽት በሲቢኤስ  የተላለፈው ይህ ታላቅ ዝግጅት እንደ ሲልቬስተር ስታሎን፣ ኪስ የሙዚቃ ባንድ፣ ጆርጅ ስትሬት፣ ማይክል ክሮፎርድ እና ግሎሪያ ጌይኖር ያሉ ዝነኛ አርቲስቶችን በክብር ዘክሯል።

ይህ የትራምፕ አስተያየት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ ክርክር የቀሰቀሰ ሲሆን፣ አንዳንዶች በቴሌቪዥን ስራ የቆየ ልምድ ያላቸው ፕሬዝዳንቱ በምርጫ ወቅትም ቢሆን ከፖለቲካው ይልቅ ለሚዲያ ስራ ያላቸውን ቅርበት እንደሚያሳይ እየገለጹ ይገኛሉ።

በተጨማሪም በታሪክ “የኬኔዲ ሴንተር” ተብሎ የሚጠራው ተቋም በቅርቡ ወደ “ትራምፕ ኬኔዲ ሴንተር” መቀየሩና ፕሬዝዳንቱ ራሳቸው በመድረኩ ላይ አቅራቢ ሆነው መቅረባቸው በፖለቲካ እና በጥበብ ሰዎች ዘንድ የተለያየ አመለካከት እንዲሰነዘር ምክንያት ሆኗል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...