ነዳጅ ያላአግባብ ያፈሰሱ አካላት እገዳ ተጣለባቸው

Date:

ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጥቶበት ወደ አገር የሚገባን ነዳጅ ኃላፊነት በተሞላው መንግድ ለህዝብ ጥቅም ማዋል ሲገባው ያለአግባብ እንዲፈስ ያደረገ ማደያ ለሶስት ወር ከነዳጅ ጭነት ትስስር እገዳ ተጣለበት፡፡

በአሪሲ ዞን ዳክሲሰ በሚባል ቦታ ሥራ የጀመረ ግሎባል የሚባል ማደያ ከነዳጅ መቅጃ ማሽን ነዳጅን ሲያርከፈክፍ በማህበራዊ ትስስር ገፆች መታየቱን ተከትሎ ባለስልጣኑ ጉዳዩን በማጣራት ድርጊቱን መፈጸሙን በማረጋገጡ ይህን ድርጊት የፈጸመው ማደያ በነዳጅ ግብይት አዋጅ ቁጥር 1363/2017 አንቀጽ 7(10)ስር ያለዉን ግዴታ በመጣስ በአንቀጽ 11(9)መሠረት ህገ ወጥ ድርጊት ፈጽሞ ስለተገኘ የወንጀል ተጠያቂነቱ የሚቀጥል ሆኖ በአዋጁ አንቀጽ 23(1)መሠረት ለ3ወራት ፈቃዱ ታግዷል፡፡

ከባለስልጣን መ/ቤቱ የማደያ ፈቃድ አውጥተው ምርቱን ለህብረተሰቡ በአግባቡ ተደራሽ ለማድረግ ፈቃድ ሲሰጥ ከሚገቡ የፈቃድ ግዴታዎች መካከል አንዱ የነዳጅ ደህንነቱን እና ደረጃውን በጠበቀ ማዳያ በቂ የሆነ የድንገተኛ አደጋ መከላከያ ግብዓቶችን አሟልቶ በወጣው የእለታዊ ዋጋ በጥብቅ ዲስፕሊን እና ጥንቃቄ ለተጠቃሚው መሸጥ ግዴታዎችን የጣሱ በመሆኑ ባለስልጣን መ/ቤቱ ጉዳዩን ተከታትሎ ተገቢው የህግ ውሳኔ ተፈጻሚ እንዲሆን ክትትል እንደሚያደረግ ያሳውቃል። ህገወጥ የነዳጅ ግብይትን የመከላከል ስራ የመላው ህዝብ ሃለፊነት በመሆኑ ይህን ድርጊት ለጠቆማችሁ ምስጋነችን እናቀርባለን።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...