ኒያላ ኢንሹራንስ ዲጂታል ኢንሹራንስና የአረቦን ፋይናንሲንግ አገልግሎት ሊጀምር ነው

Date:

ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. ፤ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ ጋር በጋራ በመሆን ዲጂታል የኢንሹራንስ እና የአረቦን ፋይናንሲንግ አገልግሎት ለመስጠት በትናትነው ዕለት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

በኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ዘርፍ ለ30 ዓመታት አገልግሎት በመስጠት የሚታወቀው ኒያላ ኢንሹራንስ ደንበኞች ወደ ኢንሹራንስ ቅርንጫፍ መሄድ ሳይጠበቅባቸው የእጅ ስልካቸውን ብቻ በመጠቀም ለንብረታቸው የመድን ሽፋን ዋስትና መግዛት የሚችሉበት ሙሉ በሙሉ ዲጂታል የሆነ አገልግሎት ለመስጠት የዲጂታል መተግበሪያ ቴክኖሎጂ አቅራቢ ከሆነው ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስና ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ጋር የጋራ ስምምነት አድርገዋል፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የአረቦን ክፍያቸውን ተበድረው መክፈል ለሚፈልጉ ደንበኞች የብድሩን ገንዘብ አቅርቦት ተደራሽ ያደርጋል።

አገልግሎቱን ግለሰብ ሆነ ድርጅት የካቻን መተግበሪያ ከፕሌይስቶር ወይም አፕስቶር ላይ በማውረድ በቀላሉ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ደንበኞች በተበደሩት መጠን ልክ ብድራቸውን በ1፤ በ3፤ በ6 ወይም በ9 ወራት በተመቻቸላቸው የጊዜ ገደብ መክፈል እንደሚችሉ እና የሚያስፈልጋቸውን የገንዘብ መጠን በብድር መልክ ማግኘት እንደሚችሉ ተጠቅሷል።

የመግባቢያ ሰነዱን በኒያላ ኢንሹራንስ በኩል አቶ ተገኝ ማስረሻ የኩባንያው ቺፍ ከስተመር ማኔጅመንት ኦፊሰር፤ ወ/ሮ መቅደስ በቀለ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ዲጂታል ባንኪንግ ዳይሬክተር፤ እንዲሁም የካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አብርሀም ጥላሁን ፈርመዋል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን የመከላከያ ስምምነቶችና የፖለቲካዊ ድጋፎች

በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣውን የጸጥታ ስጋት ተከትሎ፣ ጣሊያን ለባህረ...

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ”ንዋይ” የተሰኘ መተግበሪያን ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎች...

የነዳጅ እጥረት አሽከርካሪዎችን ለከፋ እንግልት እየዳረገ ነው

በአዲስ አበባ እና በልዩ ልዩ የክልል ከተሞች የሚስተዋለው የነዳጅ...

ሼክ ኢብራሂም ቱፋ በኢራን ኤምባሲ በመገኘት ሀዘናቸውን ገለጹ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼክ ኢብራሂም...