ኔስሊ(Nestle) የተሰኘው የህፃናት ምግብ አምራች በመላው አለም ያሉ ምርቶቹ ወደ ኩባንያው እንዲመለሱ ጠይቋል

Date:

Nestle የተሰኘው የህፃናት ምግብ አምራች ኩባንያ “SMA, BEBA, NAN እና Alfamino” የተሰኙት የህፃናት ምግቦች ላይ ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ የሚያስከትል “cersulide” ከተሰኘ ኬሚካል ጋር የተነካኩ ናቸው በማለት ምርቶቹ እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል።

ድርጅቱ መጀመሪያ ጥሪውን ያቀረበው በአውሮፓ በሚገኙ አንዳንድ ምርቶች ላይ የነበረ ቢሆንም በኋላ ላይ ጥሪውን ወደ አፍሪካ፣ አሜሪካና እስያ አስፍቷል።

ኩባንያው እስካሁን ከምግቦቹ ጋር በተያያዘ የተፈጠረ የጤና እክል እንደሌለ ቢገልጽም ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ 37 ሃገራት  ከህፃናት ምግቡ ጋር በተያያዘ የጤና ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

የብራዚል የጤና ሚኒስቴር መርዛማው ነገር የተገኘው በኔዘርላንድስ በተመረቱት ላይ ነው ሲል፣ የኔዘርላንድስ ተቋሙ በስዊዘርላንድ የተመረቱት ላይ ነው ብሏል።

የደቡብ አፍሪካ የጤና ሚኒስትር ወደ ኩባንያው እንዲመለሱ የተጠሩት ምርቶች በባለፈው ሰኔ የተመረቱና የ18 ወራት ቆይታ ያላቸው እንደሆኑ ገልጿል።

ዜናው ከተሰማ በኋላም የህፃናት የምግብ አምራቹ ኩባንያ ነስትል የአክሲዮን ዋጋ በ5.7% ቀንሷል።

Nestle ከዚህ ቀደም ወደ አፍሪካ በሚልካቸው የህፃናት ምግቦች ላይ ከመጠን በላይ ስኳር ይጨምራል ተብሎ ተከሶ ነበር።

ዘገባው የሮይተርስ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...