ለመጀመሪያ ጊዜ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እስራኤል ጦርነቱን ለማቆም እንደምትፈልግ በይፋ አምነዋል። ኔታንያሁ በዋሽንግተን እንደተናገሩት እስራኤል በዚህ የ60 ቀናት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ እና ጦርነቱን በዘላቂነት ለማቆም ድርድር ለመጀመር ፈቃደኛ መሆኗን ተናግረዋል።
ነገር ግን እስራኤላውያን በጋዛ ያለውን ጦርነት እንድታቆም አነስተኛ መስፈርቶች ብሎ የሚጠራቸው ነገሮች እንዳሉ አንስተዋል። የመጀመሪያው ሃማስ ትጥቁን እንዲያስቀምጥ ነው። ሁለተኛው ሃማስ በወታደራዊ እና በፖለቲካዊ መልኩ እንዲበታተን እንደሚፈልጉ አንስተዋል።
ሦስተኛው ሃማስ ወደፊት እንዳይቀጣ አክለዋል። ኔታንያሁ በአንድ ወይም በሌላ መንገድ እስራኤል አላማዋን ታሳካለች ፤ በእነዚያ 60 ቀናት ውስጥ እስራኤል በዲፕሎማሲያዊ መንገድ የምትፈልገውን ካላገኘች ወደ ጦርነቱ ትመለሳለች ብለዋል ።
