” አሁን በሕክምና ላይ ነው ያለሁት ፤ ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን “

Date:

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ያለፉት በዓላት በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቁ አስተዋጽኦ ለነበራቸው ሁሉ ምስጋናቸውን አቀረቡ፡፡

ቅዱስነታቸው በሸገር ሀገረ ስብከት በኮየ ፈጨ ክፍለ ከተማ በፋንታ መድኃኔዐለም ደብር የከተራ በዓል እለት  ሕይወታቸውን ላጡ ኦርቶዶክሳዊያንም ሐዘናቸውን ገልጸዋል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በክብረ በዓላቱ ያልተገኙት ባጋጠማቸው የጤና ችግር ምክንያት መሆኑንም ጠቁመው አሁን በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

ቅዱስነታቸው ባለፉት ቅዱሳት የቤተክርስቲያን በዓላት በአካል ባይገኙም ሥነ ስርዓቱቶችን ግን ከአባቶች እና ከመገናኛ ብዙሃን መከታተላቸው አስታውሰዋል፡፡

አያይዘውም ” አሁን በሕክምና ላይ ነው ያለሁት ፤ ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን ፤ በሃገር ውስጥም በውጭም ያላችሁ ወገኖቼ በእውነቱ በጣም እንዳሰባችሁ እሰማለሁ፤ ስለ ሐሳባችሁ ስለመጨነቃችሁ እግዚአብሔር ይስጥልኝ ፤ ሁላችሁም በጸሎት አስቡን ’” ብለዋል፡፡

ቅዱስነታቸው በመጭዎቹ በዓላት ልክ እንደወትሮው ሁሉ አባታዊ ቡራኬ ለመስጠት እግዚአብሔር አምላክ እንደሚያበቃቸው  ባለ ሙሉ ተስፋ መሆናቸውንም አመላክተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...