አማርኛ ለምን ከአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋዎች አንዱ ሳይሆን ቀረ ?

Date:

ፕሮፌሰር ባዬ ይማም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ልሳን ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ናቸው ፡፡ ፕሮፌሰር ባዬ አማርኛን ከአፍሪካ ህብረት የሥራ ቋንቋዎች አንዱ ለማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ምልከታቸውን ካቀረቡት መካከል ናቸው ፡፡

ተመራማሪው አማርኛ ከአፍሪካ ብቸኛው የራሱ የፁሁፍ ፊደል ያለው ቋንቋ የሆነበትን ታሪካዊና ሥነ ልሳናዊ አመጣጥ በትንተና አብራርተዋል ፡፡

ቋንቋው በ1963 ዓም የአፍሪካ ህብረት ማቋቋሚያ ቻርተር ከተፈረመባቸው ቋንቋዎች አንዱ መሆኑን የተናገሩት  ፕሮፌሰር ባዬ “ ነገር ግን ቋንቋውን ዛሬም ድረስ የህብረቱ የሥራ መገልገያ እንዲሆን ማድረግ አልተቻለም ፡፡

ለዚህ ደግሞ ውስጣዊና ውጪያዊ ምክንያቶች አሉ ፡፡ ከውስጣዊ ምክንያቶቹ ኢትዮጵያ ከህብረቱ ምሥረታ ማግሥት ጀምሮ በአብዮት እና ባልተረጋጋ ፖለቲካዊ ሁኔታ  በመጠመዷ ነው ፡፡

ይህ ውስጣዊ አለመረጋጋት ለጉዳዩ ትኩረት እንዳትሰጥ አድርጓታል ፡፡ እንዲሁም የህብረቱን መመሥረት ሥጋት የገባቸው የቀድሞ ቀኝ ገዢዎች አፍሪካዊ ማንንት እንዳይጎለብት እጃቸውን በማስገባት የራሳቸውን ተፅእኖ ማድረጋቸው ነው “ ብለዋል ፡፡


የቋንቋ ቅኝ ግዛት / Language colonialism /

ሌላው በመድረኩ ላይ ሀሳባቸውን ያቀረቡት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የስነ ልሳንና ስነተግባቦት ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር ፈቀደ ሚኖታ ናቸው ፡፡

ዶክተር ፈቀደ የወቅቱ አፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ አፍሪካ ህብረት ሲመሠረት አፍሪካዊ ማንነት በማቀንቀንና የፓን አፍሪካኒዝም መርህ ላይ የተመሠረተ ነበር ይላሉ ፡፡ ቋንቋ አንዱ የማንነት መገለጫ ቢሆንም ህብረቱ ግን ዛሬም ድረስ Anglo phone and Franko phone በተባሉ የቅኝ ገዢዎች ቋንቋ እየተገለገለ እንደሚገኝ የተናገሩት ዶክተር ፈቀደ “ አፍሪካ ነጻ ብትወጣም አሁንም በቋንቋ ቅኝ ግዛት / Language colonialism / ሥር ትገኛለች “ ብለዋል ፡፡

በቋንቋው ላይ የጋራ መግባባት

በውይይቱ ላይ የሁለቱ ሀሳብ አቅራቢዎችን ገለጻ ተከትሎ ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተዋል ፡፡ አማርኛ ከመጣባቸው ታሪካዊ ዳራዎች አንጻር እንደ ጨቋኝ ቋንቋ እና ከብሄሮች አፈና ጋር ተያይዞ የሚቀርብበት ሁኔታ መኖሩን የተናገሩት አንድ የውይይቱ ተሳታፊ “ ይህን ላለፉት ብዙ ዓመታት ሲነገር ነው የቆየው ፡፡ ይህን ተቃርኖ እንዴት ማስታረቅ ይችላል “ በማለት ጠይቀዋል ፡፡

የህብረቱ የሥራ ቋንቋ ይሁን የሚለውን እንዴት ነው ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው በማለት አስተያየታቸውን የጀመሩት ሌላው ተሳታፊ “ እኛ መጀመሪያ የቤት ሥራችንን ሰርተናል ወይ ?    ቋንቋው ላይ  ሁላችንም የጋራ  መግባባት አለን ወይ ?  “ በማለት ጠይቀዋል ፡፡

የቤት ሥራ

እንደተባለው የውስጥ የቤት ሥራችንን መሥራት እንደሚያሥፈልግ የጠቀሱት ፕሮፌሰር ባዬ ይማም ”  ህዝቡን በቋንቋ እና በባህል ማስተሳሰር ይገባል ፡፡ ልዩነትንና አንድነትን መረዳት ያሥፈልጋል ፡፡ አላስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ባይፈጸሙ ጥሩ ነበር ከተፈፁሙም ግን እሱን እያነሳን መናቆር ሳይሆን ወደ ፊት እሱን ተወት አድርገን በአገር እና በአፍሪካ ደረጃ መሥራት ባሉብን ጉዳዮች ላይ ማተኮር ይገባል “ ብለዋል፡፡

የአንዱ ቋንቋ ቀድሞ የህብረቱ የሥራ ቋንቋ መሆን ሌላው ተመሳሳይ ጥያቄ እንዳያቀርብ የሚከለከል እንዳልሆነ የተናገሩት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊና ስነሰብ ኮሌጅ ዲን ፕሮፌሰር ዘለቀ አርፍጮ በበኩላቸው  “ እንዳውም አንዱ ለሌላው በር የሚከፍት እንደሆነ አድርጎ ማየት ይገባል “ ብለዋል ፡፡

DW

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አርሰናል ከቦርንማውዝ በጉጉት የሚጠበቅ ጨዋታ

በ32ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ቀን...

በአሜሪካ እና ኢራን ድርድር ላይ የሚነሱ አራት ቁልፍ ጥያቄ

በፓኪስታን የሚደረገው የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር እየተጠበበፓኪስታን ነገር ግን...

መንገዳችን ረጅም፣ ጉዟችን ፈታኝ መሆኑን እናውቃለን

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል...

የተመድ ዋና ጸሐፊ ኢራን እና አሜሪካ “በቅን ልቦና” ወደ ድርድሩ እንዲገቡ ጠየቁ

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አሜሪካ እና ኢራን...