አሜሪካ ተወገዘች

Date:

አሜሪካ በቬንዙዌላ ላይ የምታደርሰው ጫና እንዲሁም የመውጣትና መግባት  ገደብ የመጣል አካሄድ  ህገ ወጥ ነው በሚል የመንግስታቱ ድርጅት ባለሙያዎች ከሰሱ።

ህገ ወጥ ወታደራዊ እርምጃ ነው በሚል አራት የድርጅቱ ባለሙያዎች ወቅሰዋል።

የአሜሪካ ኮንግረስ በጉዳዩ ላይ ጣልቃ እንዲገባም ጠይቀዋል።

አንድን አገር በጦር ዘግቶ አንድ ወገናዊ ማዕቀብ መጣል መብት እንዳልሆነም አሳስበዋል።

ባለሙያዎቹ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ተቀባይነት የሌለው ድርጊት ነው በሚል አውግዘዋል፤ጣልቃ ሊገባበት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

አሜሪካ ጦሯን በካሪቢያን እና ፓስፊክ ውቅያኖስ በማስፈር የቬንዙዌላ መንግስት ላይ ጫና እየፈጠረች ነው።

አንድን አገር እንዳይወጣና እንዳይገባ መዝጋት በመንግስታቱ ድርጅት ቻርተር የተከለከለ ነውም ተብሏል።

የጠቅላላ ጉባዔው የ1974 ትርጓሜም ህገ ወጥ ተግባር ነው በሚል ደንግጓል።

አሜሪካ የኒኮላስ ማዱሮ መንግስት
በህገ ወጥ የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ስራ ላይ ተሰማርቷል በሚል በዓለም አቀፉ የውሀ አካል ላይ ጥቃት መሰንዘር ከጀመረች አራት ወራት ሆኗታል።

አልጀዚራ እንዳስነበበው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...