በ2ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አርሰናል ሊድስ ዩናይትድን 5 ለ 0 አሸንፏል፡፡
በጨዋታው የመድፈኞቹን ግቦች የክረምቱ ፈራሚ ቪክተር ዮከሬሽ (2) ፣ ዩሪየን ቲምበር (2) እና ቡካዮ ሳካ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
ከጨዋታው መጀመር አስቀድሞ አዲሱ የአርሰናል ፈራሚ ኤቤሬቺ ኤዜ በኢምሬትስ ከደጋፊዎች ጋር ተዋውቋል፡፡
በሌሎች የዛሬ መርሐ ግብሮች ቦርንማውዝ ወልቭስን፣ ብሬንትፎርድ አስቶን ቪላን በተመሳሳይ 1 ለ 0 እንዲሁም በርንሌይ ሰንደርላንድን 2 ለ 0 በማሸነፍ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ድላቸውን አሳክተዋል፡፡
