በኮንስትራክሽን ሥራ ከተሰማራ 17 ዓመት ያስቆጠረውና አሁን ላይ በሪል እስቴት ሥራ ሦስት ዓመት የሆነው አልቲማ ሪል እስቴት፤ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህን ብራንድ አምባሳደሩ አድርጎ ሾሟል።
በግንባታ ዘርፍ ረጅም ዓመታትን ያስቆጠሩ የግንባታ ባለሙያዎች የመሰረቱት ሪል እስቴቱ፤ “ሕልምዎን ይኑሩ” በሚል መሪ ቃል ቤቶችን እየገነባ እንደሚገኝ አስታውቋል።
በሦስት ዓመታት ሁለት ግንባታዎችን አጠናቆ ያስረከበ ሲሆን፤ አንድ ግንባታው ደግሞ ለመጠናቀቅ 80 በመቶ በላይ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።
አልቲማ ሪል እስቴት ባለ 2ዐ ወለል ግንባታ በመስቀል ፍላወር ቱሊፕ ኦሎምፒያ ጎን ያስጀመረ ሲሆን፤ በማስታወቂያ፣ ፊልም እና ቴአትር ላይ ተወዳጅነት ያለውን አርቲስት ነፃነት ወርቅነህን የድርጅቱ የአልቲማ ሪል ስቴት የብራንድ አምባሳደር በማድረግ ስምምነት ፈጽሟል።
የዜጎችን የቤት አቅርቦት ችግርን ለመቀነስ እየሰራ እንደሚገኝ የአልቲማ ሪል እስቴት ተናግሯል።
በአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት አቅርቦት እጥረት ችግርን ለማቅለል ለዜጎች በተመጣጣኝ ዋጋ ቤቶችን እያቀረበ እንደሚገኝና ለማቅረብ እንደሚስራም አስታውቋል።
አልቲማ ሪል እስቴት በስትራቴጂ ደረጃ በሚመጡት 10 ዓመታት ከ15 ፕሮጀክቶች በላይ ለመሥራት ፕላን ይዞ እየተንቀሳቀስን እንደሚገኝና ከ2 ሚሊዮን 700 ሺሕ ብር ጀምሮ እስከ ትልቅ ገንዘብ ድረስ የመኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት ማቀዱን ጠቅሷል።
በዚህ 3 ዓመት ጊዜ ውስጥ ሁለት ፕሮጀክቶችን መቶ በመቶ በመጨረስ፤ አንድ ፕሮጀክት ደግሞ ከ80 በመቶ በላይ እየገነባ እንዳለ ጠቁሟል።
ከ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ጀምሮ ቤቶችን እስከ ትልቁ እስከ 30 ሚሊዮን ድረስ የመኖሪያ ቤቶችን ለሽያጭ ማቅረቡን አብራርቷል።
ሪል እስቴቱ በአጠቃላይ የዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች የቤት ባለቤት ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ ነው ያስታወቀው። ከአቅርቦት በተጨማሪ የዜጎችን ገቢ መሰረት በማድረግ እንደሚሰራ ተገልጿል።
ይህም ከሌሎች የቤት አልሚዎች አልቲማ ሪል እስቴትን እንደሚለየው ተነግሯል።
(አሐዱ ሬዲዮ)
