አሰቃቂውን ጥቃት የፈጸሙ ተጠያቂዎች ለፍትሕ እንዲቀርቡ ፓትርያርኩ ጠየቁ

Date:


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በቦረና ወረዳ በግዮን አባይ ገዳመ አስቄጥስ ቅድስት አርሴማ፣ አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶችና የእናቶች አንድነት ገዳም ላይ ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. በተፈጸመው ጥቃት ላይ መግለጫ አውጥተዋል።

በመግለጫቸው፣ በጥቃቱ የመናንያን መነኮሳይያት ሕይወት በግፍ መጥፋቱን፣ በርካቶች መቁሰላቸውን እና በገዳሙና በንዋየ ቅድሳቱ ላይ ውድመት መድረሱን ከሀገረ ስብከቱ መግለጫ በከፍተኛ ሐዘን መስማታቸውን ገልጸዋል።

በተመሳሳይም፣ በዚሁ ዕለት በሀድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት የአምልኮ ሥፍራ በኃይል መፍረሱና በምእመናን ላይ ጥቃት መድረሱ በመግለጽ ድርጊቱ የሚያሳዝንና በፍጹም ተቀባይነት የሌለው የተወገዘ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

ፓትርያርኩ እንዳሉት፣ የጸሎት፣ የትምህርት፣ የሰላምና የመንፈሳዊ እሴት ማዕከል የሆኑትን ገዳማት መጠበቅ የአንድ ሃይማኖት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ የሰው ልጅ ክብርን፣ የሕግ የበላይነትንና የሀገር ሰላምን የማስጠበቅ ኃላፊነት ያላቸው በየደረጃው የሚገኙ ባለሥልጣናትና የሕግ አስከባሪ አካላትም የሚመለከታቸው ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል።

አሰቃቂውን ጥቃት የፈጸሙ ተጠያቂዎች ለፍትሕ እንዲቀርቡ፣ ሌሎች ገዳማትና አድባራት ደኅንነታቸው እንዲጠበቅ እና ለተጎዱትም ተገቢው ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

በመጨረሻም፣ ሕዝበ ክርስቲያንና መላው ኢትዮጵያውያን የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት ወገኖች ጋር በመንፈሳዊም ሆነ በስብአዊ ድጋፍ እንዲቆሙ አሳስበው፣ ለተበደሉት ፍትሕ፣ ለቆሰሉት ፈውስ፣ በግፍ ሕይወታቸውን ለተነጠቁት ዕረፍተ ነፍስ፣ ለቤተ ክርስቲያኒቱና ለሀገሪቱ ፍጹም ሰላም እንዲሰጥ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት ገለጸች

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት የአገሪቱ...

ከትግራይ ዩኒቨርሲቲ ታጣቂዎች ካልወጡ ተማሪ አንመድብም

ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል የሚገኙ መቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና...

ኢራን አሜሪካ የጣለችባት ዕገዳ የበለጠ የሚጎዳው ዋሽንግተንን ነው አለች

አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው የኢኮኖሚ እና የባሕር እንቅስቃሴ እገዳ...

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...