አቶ ሙሼ ሰሙ ስለ ትምህርት ፓሊሲዉ ምን አሉ

Date:

ከአራት ዓመት በፊት ተግባር ላይ የዋለው የትምህርት ፓሊስ ከዓመት ወደ ዓመት “የድሃ ልጅን” ከከፍተኛ የትምህርት ስርዓት እያስወጣ የመካከለኛና ከፍተኛ ገቢ ያለውን “የሀብታም ልጅ” ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በስፋት የማስግባት እድል እየፈጠረ በመሆኑ “ማህበረሰባችን ተረጋግቶ እንዳይኖር ሊያደርግው” እንደሚችል ትምህርት ሚኒስትሩ ለቋሚ ኮሚቴ ስጋታቸውን ሲገልጹ አደመጥኩ።

ቃል በቃል በሪፓርታቸው እንዳቀረቡት ። እኔን በጣም የሚያሳስበኝ” በማለት የጀመሩት ሚኒስትሩ… “በሃብታምና በድሃ መካከል ያለው ልዮነት በኢኮኖሚ [ያዊ ጉዳይ] እንዳለ ሆኖ የወደፊት ሕይወቱን በሚወስነው ትምህርት ላይእንደዚሁ ያንን ሚረር (Mirror) የሚያደርግ ልዩነት ከተፈጠረ አንድ ህብረተሰብ ተደላድሎ መኖር አይችልም” ሲሉ አደጋና መዘዙን በአሳሳቢ ቋንቋ ገልጸውታል።

የተደቀነውን “የድሐ ሀብታም ልዩነት” አደጋ አስመልክቶ ላለፉት 4 ዓመታት ከፍተኛ ትምህርት የኢሊት (Elite) ብቻ የመሆን አሳሳቢ አደጋ የመደቀኑን ስጋት በተደጋጋሚ ሐሳቦች ቢቀርቡም በጊዜ ለመታረም ፍላጎት በመታጣቱ ምክንያት ላለፉት 4 ዓመታት ከ2 ሚሊየን የሚበልጡ የድሃ ልጆች ከከፍተኛ ትምህርት ስርዓት መገለላቸው ይታወቃል።

መራራው ሃቁ ይህ ቢሆንም የችግሩ መንስኤ ፓሊሲያቸውና በፓርላማ ፊት ቃለ መሐላ የፈጽሙለት ተቋም መሆኑንና የመፍትሔውም ባለቤት ተቋማቸው ሊሆን እንደሚገባ ማመን ያዳገታቸው ሚኒስትሩ እንደ ተለመደውም ሁሉንም ነገር ወደ ሕዝብና ቤተሰብ ላይ መወርወራቸው ይበልጥ የሚያሳስብ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

ሰሞኑንም እንደ መፍትሔ የተወሰደው ቤተሰብን ያላማከለ የግል ተማሪዎችንና የመንግስት ተማሪዎችን በአስገዳጅ ሁኔታ ቀላቅሎ የማስተማር፣ የማጥኛና የእረፍት ጊዜ በሚያሳጣ መልኩ ቅዳሜና እሁድ እንዲማሩ ማስገደድ ዛሬም ከስህተት ወደ ሌላ ስህተት ከመሸጋገር ያለፈ ለውጥ እንደማያመጣና በቤተሰብ ዘንድ እየፈጠረ ያለው መጠነ ሰፊ ጭንቀትና ተቀባይነት ማጣት በቂ መገለጫ ነው።

በጥቅሉ አሁንም የአራት ዓመት ተሞክሮ ያገኘውን ፓሊሲ በመፈተሽ ቤተሰብን መምህርንንና ት/ቤቶችን ያማከለ፣ ምክክርና መግባባት የተደረሰበት ዘለቄታ ያለው መፍትሔ ከማቅረብ ይልቅ በተወታተፈና ጥገናዊ በሆነ መንገድ ለውጥ የሚደረገው ሙከራ ትርጉም የሌለው፣ በቤተሰብና በልጆች መሐል ቤተሰባዊ መስተጋብርን የሚያጠብ ከመሆኑም በላይ ወጥነት በሌለው መንገድ በየዓመቱ የሚነባበረው ተለዋዋጭ አቅጣጫ በተማሪዎች ዘንድ ተስፋ መቁረጥና ትምህርት መጥላትን የሚያስከትል መሆኑ ሊታወቅና ሊታረም የሚገባ ነው።

የቋሚ ኮሚቴው ሪፓርት ለማዳመጥ ማስፈንጠርያውን በድጋሚ ይጨቁ

በዚህ ጉዳይ ላይ ከዚህ ቀደም ያቀረብኩትን ስጋትና የትኩረት አቅጣጫ ቀንጭቤ ከስር አቅርቤዋለሁ። ሙሉውን ለማንበብ ማስፈንጠርያውን ይጨቁኑ።

https://www.facebook.com/share/p/1GaKD1Bhhc/

“ከዚህ በላይ የሚያሳስበው ነገር በቀረበው ግርድፍ መረጃ መሰረት ኢንተርናሽናል ት/ቤቶች 85%፣ የግል ት/ቤቶች ከ50% በላይ [ የተሟላ የትምህርት ግብአት፣ የምገባ ስርዓት፣ የተሟላ ማደርያ ስፍራ፣ የጥናት ቦታና ሌሎች ተጽእኖዎች እንደ ቤተሰብ መርዳት የሌለባቸው፣ ልዩ ድጋፍና ስልጠና ያላቸው አዳሪ ት/ቤቶች] 100% ማሳለፋቸውና በተቃራኒው በርካታ የአርሷ አደርና የአርብቶ አደር ልጆች የሚማሩባቸው የመንግስት ት/ቤቶች 5% ገደማ ተማሪ ማሳለፋቸው ጉዳይ ነው።

ይህ የሚስረዳን ነገር ቢኖር ስርዓት ትምህርቱና የፈተናው ውጤት ከዓመት ወደ ዓመት ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ በኑሯቸው አቅመ ደከማ የሆኑ ቤተሰብ ልጆችን ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መገለላቸው ተጠናክሮ የመቀጠሉ ክስተት አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ነው።

በዚህ መሰረትም “አዲስ” የተባለለት ስርዓተ ትምህርት ድሃና ሀብታምን ሳይለይ ትምህርትን በአንጻራዊነት በእኩል ደረጃ ለሁሉም ማዳረስ፣ ማስፋፋትና ሚዛናዊ ዉጤትን ማስጠበቅ ሲኖርበት በአጼ ሐይለ ስላሴ ዘመን እንደ ተዘመተበት (Secter Review) ትምህርት በተለይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የአርሶ አደርና የአርብቶ አደር ልጆችን ዳር በማስያዝ ከፍተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ወላጆች ልጆችን ቀጣይነት ባለው መንገድ ባለመብት የሚያደርግና በዚሁ መንገድ ውጤቱ እየተዛባና እያገለለ እንደሚቀጥል እየተዘገበ አለማስደንገጡና አለማወያየቱ አስደማሚ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

በአጠቃላይ የትምህርት ስርዓቱ የአራት ዓመት ግምገማ የተማሪ ጥራትና የቁጥር እድገት ያልታየበት፣ የመማር ማስተማር፣ የተማሪና የመምህራን ጥመርታ ያልተሰናሰለበት፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የአርሶ አደር፣ የአርብቶ አደርና የከተማ ነዋሪ ልጆች በከፍተኛ ደረጃ ከከፍተኛ ትምህርት ተጠቃሚነት በማግለል ጥግ ያስያዘና በ4 ዓመት ውስጥ ከ2 ሚሊየን በሚበልጡ ወጣቶችን መነሻና መዳረሻ ያሳጣ ሆኗል። “

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አርሰናል ከቦርንማውዝ በጉጉት የሚጠበቅ ጨዋታ

በ32ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ቀን...

በአሜሪካ እና ኢራን ድርድር ላይ የሚነሱ አራት ቁልፍ ጥያቄ

በፓኪስታን የሚደረገው የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር እየተጠበበፓኪስታን ነገር ግን...

መንገዳችን ረጅም፣ ጉዟችን ፈታኝ መሆኑን እናውቃለን

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል...

የተመድ ዋና ጸሐፊ ኢራን እና አሜሪካ “በቅን ልቦና” ወደ ድርድሩ እንዲገቡ ጠየቁ

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አሜሪካ እና ኢራን...