አቶ አበበ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት በጡረታ ሊሰናበቱ ነው

Date:

​በዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) የአፍሪካ መምሪያ ዳይሬክተር የሆኑት ኢትዮጵያዊው አቶ አበበ አእምሮ ስላሴ፣ ከግንቦት ጀምሮ ኃላፊነታቸውን እንደሚለቁ ተገልጿል።

አቶ አበበ ድርጅቱን በፈረንጆቹ 1994 የተቀላቀሉ ሲሆን፣ ላለፉት 32 ዓመታት በተለያዩ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል።

ከ2016 ጀምሮ የድርጅቱ  ደግሞ የአፍሪካ መምሪያ ዳይሬክተር በመሆን ሰርተዋል።

በቆይታቸውም አፍሪካ በኮቪድ-19 እና በኢኮኖሚ ቀውስ ወቅት የነበሩባትን ፈተናዎች እንድትወጣ ረድተዋል።

በተለይም ለሰሃራ በታች አፍሪካ የሚሰጠውን ድጋፍ በማሳደግና በቦርዱ ውስጥ የአህጉሪቱ ድምፅ እንዲጎለብት በማድረግ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።

​የIMF ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂየቫ፤ አቶ አበበ ላሳዩት ጥንካሬ፣ ስትራቴጂካዊ አመራርና ለድርጅቱ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...