የኤሌክትሪክ የጭነት መኪኖችን ለገበያ ቀረበ
አናሀማ ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ቅዳሜ ጥር 16 2018 ዓ.ም ከጉዳዩ ጋር ቀረቤታ ያላቸው ባለሙያዎችና የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሂዷል ።
አናሀማ ትሬዲንግ በአለም አቀፍ ደረጃ በኮንስትራክሽን ዘርፍ 3ኛ ደረጃ ከያዘው XCMG ብራንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመዋል።
በመቀጠልም በፕሮግራሙ መሠረት መኪኖቹ ሲገጣጠሙ የሚያሳዩና የአናሀማን እና የXCMG የሥራ ሂደት የሚያብራሩ አጫጭር ዶክመንተሪዎች የታዩ ሲሆን የሪቫን ቆረጣ ሥነ ሥርዓትም ተካሂዷል።
ኩባንያው በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮንስትራክሽን ዘርፍ 3ኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው XCMG ብራንድ ጋር በመተባበር፣ ከ5 ቶን እስከ 20 ቶን የሚመዝኑ የኤሌክትሪክ ቫን እና የደረቅ ጭነት መኪኖችን ለገበያ አቅርቧል።
እነዚህ መኪኖች በሀገር ውስጥ በከፊል የሚገጣጠሙ ናቸው ። የ5 ዓመት የባትሪ ዋስትና ተካቶላቸዋል፣ ለገዢዎች እስከ 70% የሚደርስ የባንክ ብድር መመቻቸቱም ተገልጿል።
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስትር ድኤታ አቶ በርኦ ሀሰን እንደገለጹት፤ መንግስት ለነዳጅ ድጎማ የሚያወጣውን ከፍተኛ ወጪ ለመቀነስና ከአካባቢ ብክለት ለመላቀቅ ታዳሽ ኃይል ላይ ለሚሰሩ ተቋማት ልዩ ትኩረትና ድጋፍ ይሰጣል።
አናሀማ የመንግስትን ስትራቴጂ በመደገፍ ቀዳሚ ሆኖ መገኘቱንም ሚኒስትር ድኤታው አድንቀዋል።አያይዘውም ለድጎማ የሚወጣው ወጪ በርካታ ፕሮጀክቶችን መስራት የሚያስችል መሆኑ የሚያስቆጭ ሲሆን በአካባቢ ብክለት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያመጣ መሆኑም የሚታወቅ ነው።
መንግስታችን ይሄንኑ ታሳቢ በማድረግ ከጥገኝነት ለመላቀቅና ታዳሽ ሀይል ላይ በልዩ ትኩረት ለመሥራት ቁርጠኛ ነው ያሉት ሚንስትር ድኤታው እንደ አናሀማ ያሉ የመንግስትና የህዝብን መሻት በመረዳት የመንግስትን ስትራቴጂ የሚደግፍ ሆኖ መገኘቱ የሚበረታታ ነው ብለዋል።
በዚህ ዘርፍ ላይ የሚሰሩትን መንግስት በልዩ ትኩረት እንደሚደግፍ በማረጋገጥ በስራችሁ ኮርተንባችኋል፤ ለውጤታማ ሥራችሁ እንኳንም ደስ አላችሁ ብለዋል።
የአናሀማ መስራቹ አቶ ሀብታሙ አለማየሁ ከባለቤታቸው ጋር በመሆን የኮንስትራክሽኑን ዘርፍ በዘመነ መንገድ ለመምራት አልሞ የተነሳ ፤ ዘመኑን የዋጀ ሀሳብ ይዞ ላለፉት 15 አመታት በጽናት የቆመ ሀገር በቀል ድርጅት ነው።
አናሀማ ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር በማሽነሪ ኢምፖርት፣ ኤክስፖርት እና በማሽነሪ ኪራይ የተሰማራና የክልል መንገድ ሥራዎች ፣ ኮሪደር ልማት እና ሌሎች ትላልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ ተሠማርቶ ለሀገር እድገት የራሱን አሻራ በማኖር ላይ የሚገኝ ነው።
እንደ አባይ ግድብ እና የጫካ ፕሮጀክት ባሉ ታላላቅ ሥራዎች ላይ አሻራውን ያሳረፈ ድርጅት ነው።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ የየካ ክፍለ ከተማ ተስፋ ብርሃን ቁጥር 12 የምገባ ማዕከል ላይ በወር 6,000 በዓመት 72,000 አቅምና ረዳት የሌላቸው ሰዎችን በመመገብ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ።
ወደፊት የማዕድን ማውጣት ፣ የ5 ኮከብ ሆቴል ግንባታ እና የምግብ ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎችን ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቋል።
አጠቃላይ በቢዝነሱ ዓለም 30 አመት የቆየው አናሀማ በተለይም ኤክስካቫተሮችንና የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን ለመንግሥታዊና መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ሲያቀርብ ቆይቷል።
በ2017 ዓ.ም ብቻ ወደ 200 ኤክስካቫተሮችን ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ማምጣት የቻለ ተቋም ነዉ ።
