አንጋፋው ጋዜጠኛ በላይ በቀለ በፅኑ ታሞ በሆስፒታል ይገኛል፤የድጋፍ ጥሪ ቀረበ

Date:

በማራኪ የዜና ዘገባና በልዩ የዜና አቀራረብ ስልቱ የሚታወቀው አንጋፋው ጋዜጠኛ በላይ በቀለ ድንገተኛ የስትሮክ አደጋ አጋጥሞት፣ በአሁኑ ወቅት ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል በፅኑ ሕሙማን መከታተያ ክፍል (ICU) ውስጥ እየታከመ ይገኛል።

ጋዜጠኛ በላይ በቀለ በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ውስጥ ለበርካታ ዓመታት በሬዲዮና በቴሌቪዥን በብቃት ያገለገለ አንጋፋ ባለሙያ ነው። በቅርብ ዓመታትም “በላይ ሚዲያ” የዩቲዩብ ቻናልን በመመስረት፣ በሥራ ፈጠራ፣ በቢዝነስና በግል ልማት ዙሪያ ለወጣቶች እውቀትና ልምድ ሲያካፍል ቆይቷል።

ከጋዜጠኛው የቅርብ ወዳጅ አንጋፋው ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ በተሰጠ መረጃ መሠረት፣ የስትሮክ አደጋው ከተከሰተ በኋላ ወደ ልዩ የስትሮክ ሕክምና ማዕከል ለማዛወር ጥረት ተደርጎ ነበር። ሆኖም ከአደጋው ጀምሮ ከ24 ሰዓት በላይ በመቆየቱ ምክንያት የቀዶ ሕክምና አማራጩ ወሳኝ ጊዜ ማለፉን ሐኪሞች እንደገለጹ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል የሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች አስፈላጊውን የነፍስ አድን ሕክምናና የቅርብ ክትትል እያደረጉለት ነው።

ይህ ሕይወቱን ሙሉ ለሕዝብ መረጃና እውቀት ሲያበረክት የኖረ አንጋፋ ባለሙያ ዛሬ የወገኖቹን እገዛ የሚሻበት ወቅት ላይ ይገኛል።

የድጋፍ ጥሪ

ለጋዜጠኛ በላይ በቀለ የሕክምና ወጪ ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ፦

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)
የአካውንት ቁጥር፦ 1000191873061
የአካውንት ስም፦ የላይ አለማየሁ በፍቃዱ

በጸሎት፣ በማበረታታትና በምንችለው የገንዘብ ድጋፍ ከጋዜጠኛ በላይ በቀለና ከቤተሰቦቹ ጎን እንቁም።

እግዚአብሔር ሙሉ ጤንነቱን ይመልስለት!

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

መልካም አዲስ ዓመት!!

  ግዮን መጽሔት :-   አዲሱን የኢትዮጵያ ዓመት ስንቀበል፣ ለውዷ ኢትዮጵያችንና...

የድሬዳዋ አስተዳደር ተሿሚዎች

4ኛ የስራ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት፣ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ያካሄደዉ...

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ተሿሚዎች

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ  ክልል ምክር ቤት 7ኛ የስራ ዘመን፣ 1ኛ...

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ተሿሚዎች

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 7ኛ የስራ...