አዲስ አበባ የአፍሪካ የሎጂስቲክስ ማኅበር ዋና መቀመጫ ሆና ተመረጠች

Date:

በቱርክ ኢስታንቡል እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ የሎጂስቲክስ ማኅበራት ጉባኤ፥ አዲስ አበባ ከተማን የማኅበሩ ዋና መቀመጫ አድርጎ መምረጡ ተገለጸ።

ይህን የገለጹት ኢትዮጵያን ወክለው በጉባኤው ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የኢትዮጵያ የዕቃ አስተላላፊዎችና የመርከብ ወኪሎች ማኅበር አቶ ዳዊት ውብሸት ናቸው።

በቱርክ እየተካሄደ በሚገኘው ጉባኤ ላይ 35 ሀገራት ተሳታፊ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ዳዊት ውብሸት፥ ኢትዮጵያ የቦርድ ወንበር ማግኘቷንም ይፋ አድርገዋል።

የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ይህን ያስታወቁት የሎጂስቲክስ እና ትራንስፖርት ዘርፍ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና የዩኒቨርሲቲዎች የጋራ የምክክር መድረክ እየተከናወነ በሚገኝበት መድረክ ላይ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

ኢትዮጵያ በ2027 የሚካሄደውን የዓለም የእቃ አስተላላፊዎችና የመርከብ ወኪሎች ማህበር (ፊያታ) ጠቅላላ ጉባኤን በመዲናዋ አዲስ አበባ እንደምታስተናግድም ተገልጿል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ትራምፕ የኢራን የኒውክሌር ተቋም ላይ ጥቃት ለማድረስ ዛቱ

አሜሪካ በኢራን ላይ የምታደርሰው ጥቃት 11ኛ ቀኑን ይዟል። ፕሬዝዳንት...

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአሜሪካ ” American Space ” ማዕከል ተመረቀ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቨን ማሲንጋ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተቋቋመውን "American...

አሐዱ ባንክ ለ 8ኛ ጊዜ የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናወነ

አሐዱ ባንክ ሥራ የጀመረበትን 4ኛ ዓመት በማስመልከት የተለያዩ ኩነቶችን...

ዕንባ ጠባቂ ከቀረቡለት አቤቱታዎች 84% በመንግስታዊ ተቋማት ላይ የቀረቡ ናቸው

የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በተጠናቀቀው የ2018 በጅት ዓመት...