አዲስ የታሪክ ማስታወሻ መጽሐፍ ተመረቀ

Date:

ታዋቂው ደራሲና የቀድሞ የትግል አባል ካህሳይ አብርሃ ብስራት (አማኑኤል ማንጁስ)፣ “ያልተመለሱ ዳናዎች – የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ሠራዊት (ኢሕአሠ) ትዝታና ኩርባዎች” በሚል ርዕስ ያዘጋጁት አዲስ መጽሐፍ በብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ (ወመዘክር) አዳራሽ በድምቀት ተመርቋል።

መጽሐፉ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ታሪክና የኢሕአሠ የትግል ጉዞ፣ የነበሩ ትዝታዎችንና የታሪክ ኩርባዎችን በዝርዝር የሚቃኝ ነው።

ደራሲ ካህሳይ አብርሃ ቀደም ሲል “የአሲንባ ፍቅር” በተሰኘው መጽሐፋቸው በአንባቢዎች ዘንድ ከፍተኛ እውቅናን ያተረፉ መሆናቸው ይታወሳል።

ይህ መጽሐፍ ለትውልድ የሚጠቅም የታሪክ ሰነድ ሆኖ እንዲያገለግልና በወቅቱ የነበሩ እውነታዎችን ለንባብ ለማብቃት ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

በምረቃው ወቅት እንደተገለጸው፣ መጽሐፉ በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ላይ የራሱን አሻራ የሚያሳርፍና ለተመራማሪዎችም ሆነ ለታሪክ ወዳዶች ጠቃሚ መረጃዎችን የያዘ ነው።

በጌጡ ተመስገን ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን አዘጋጅነት በተከናወነው በዚህ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ  ታዋቂ ግለሰቦች፣ የጥበብ ሰዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ እና የቻይና አየር መንገዶች የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ቻይና ሳውዘርን አየር መንገድ በቻይና...

ሁቲዎች በሳዑዲ የነዳጅ ኩባንያ አስተዳደር ሕንጻ ላይ በፈጸሙት ጥቃት በእሳት ተያያዘ

የሳዑዲ አረቢያ የኢነርጂ ሚኒስቴር በአገሪቱ ምሥራቃዊ ግዛት የሚገኘው ከዓለም...

የሹመት ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  ሹመት የሰጧቸው አመራሮች፡- 1. አቶ...

እንደዚህ ዓይነቱ ብልሹ ኣሰራርን ካላረምን በቀር መልካም ኣስተዳደርን …

በኣጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኣጠቃላይ...