አዲስ የኤችአይቪ መከላከያ መድኃኒት ጥቅም ላይ ሊዉል ነዉ

Date:

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በቅርቡ የጸደቀውን የኤችአይቪ መከላከያ መድኃኒት “ሌናካፓቪር” (Lenacapavir) ኤችአይቪን ለመዋጋት በሚደረገው ጥረት ውስጥ አገሮች እንደ  መሳሪያ እንዲጠቀሙበት ምክረ ሃሳብ ማቅረቡን ሲኤንኤን (CNN) ዘግቧል።

ይህ መድኃኒት በተለይም ለቫይረሱ ተጋላጭ ለሆኑ ቡድኖች እና የኤችአይቪ ስርጭት ከፍተኛ በሆነባቸው አካባቢዎች ቅድሚያ እንዲሰጠው ተመላክቷል።

የዓለም ጤና ድርጅት ይህንን አዲስ መድኃኒት በይፋ እውቅና ሰጥቶ በተግባር ላይ እንዲውል ማረጋገጫ ቢሰጥም፣ መድኃኒቱ ወደ አፍሪካ እና ሌሎች ታዳጊ አገራት የሚደርስበት ጊዜ እስካሁን ግልጽ አለመሆኑ ተጠቁሟል።

ይህ አዲስ መድኃኒት የኤችአይቪ ስርጭትን ለመግታት በሚደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት ውስጥ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል።

የዓለም ጤና ድርጅት የሰጠው ምክረ ሃሳብ አገራት የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ የሚጠቀሙባቸውን የመከላከያ ዘዴዎች ለማስፋት ይረዳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አዲስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ኢራን የበለጠ ምላሽ በመስጠት የተራዘመ ጦርነት እንደምታካሂድ አስታወቀች

ከፍተኛ የኢራን ወታደራዊ ባለሥልጣናት አሜሪካ ሌላ ዙር ጥቃት በአገራቸው...

ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በሥራ ቡድን ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘውን...

የጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ 28 የውጭ ዜጋ ተማሪዎችን ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ጋር ማስተሳሰሩን ገለጸ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ መርሃ-ግብር አማካኝነት በዘንድሮው ዓመት...

የሕግ ተማሪዎቹ አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፍ የምስለ-ችሎት ፍጻሜ አለፉ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በአህጉራዊው የዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት...